Featured

አስፈላጊነት ብቁና ውጤታማ አስተዳደር እንዲሰፍን የአስተዳደር መ/ቤቶች በህግ የተሰጣቸውን ስልጣን፣

አስፈላጊነት ብቁና ውጤታማ አስተዳደር እንዲሰፍን የአስተዳደር መ/ቤቶች በህግ የተሰጣቸውን ስልጣን፣ ተግባርና ግዴታ በተጨባጭ ማሳካት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

አስፈላጊነት ብቁና ውጤታማ አስተዳደር እንዲሰፍን የአስተዳደር መ/ቤቶች በህግ የተሰጣቸውን ስልጣን፣ ተግባርና ግዴታ በተጨባጭ ማሳካት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

ስኬት እንዲኖር ደግሞ የማስፈፀም ስልጣን ብቻውን በቂ አይሆንም፡፡ ጠቅለል ያለ ይዘት ያላቸው በፓርላማ የሚወጡ ህጐች የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ከመጠቆም ባለፈ ቴክኒካልና ዝርዝር ጉዳዮችን ስለማይዳስሱ በየጊዜው ለሚነሱ ችግሮች ወቅታዊና ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ይሳናቸዋል፡፡ ስለሆነም አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን አስፈላጊነት ከሁለት አቅጣጫዎች ማለትም ከአስተዳደር ስራ ውጤታማነት እና ከህግ አውጭው ውስንነት አንፃር ሊቃኝ ይችላል፡፡አስፈላጊነቱ ጎልቶ ቢታይም በመስኩ ሊቃውንት ጠንካራ ተቃውሞ ሳይገጥመው አልቀረም፡፡ እንደ ብዙዎች እምነት የአስተዳደር መ/ቤቶች ህግ የማውጣት ስልጣን በዜጐች መብት ላይ በሩን ዘግቶ ወደ አምባገነናዊነት የሚያመራ አደገኛ አካሄድ ነው፡፡ ተቃውሞው መሰረቱ ንድፈ ሀሳባዊ ሲሆን የስልጣን ኢ-ተወካይነት ንድፈ ሀሳብ (theory of non delegability of power) አንዱ ነው፡፡ በላቲን potestas delegari non potest delegare ተብሎ ሲጠራ በእንግሲዝኛው power once delegated should not be re-delegated የሚል ይዘት አለው፡፡ ይህም ወደ አማርኛ ሲመለስ ‘በውክልና የተሰጠ ስልጣን እንደገና በውክልና ሊተላለፍ አይችልም’ እንደ ማለት ነው፡፡ በአጭር አገላለፅ ህግ አውጭው ህግ የማውጣት ስልጣኑን የሚያገኘው ከመራጩ ህዝብ እንደመሆኑ ይህን በአደራ የተቀበለውን ስልጣን እንደገና (በድጋሚ) በውክልና ማስተላለፍ የለበትም ማለት ነው፡፡aየህግ አውጭነት የስልጣን ምንጩ ህዝብ ነው፡፡ የአንድ አገር ህዝብ ተወካዮቹን ሲመርጥ ችሎታና ብቃታቸውን መሰረት አድርጐ ‘ያስተዳድሩኛል፤ ለእኔ ይሰሩልኛል፣ ትክክለኛውን ህግ ያወጡልኛል’ በሚል እምነት ጥሎባቸው ነው፡፡ ህግ አውጭው በውክልና በአደራ ከህዝቡ የተቀበለውን ስልጣን በአግባቡ በመገልገል ልማት፤ እድገት፤ ፍትህ፣ መልካም ስርዓትና ሰላም የሚያሰፍኑ ህጐችን ማውጣት አለበት፡፡ ህዝቡ ድምፁን ሰጥቶ ተወካዮቹን ሲመርጥና ስልጣን ሲሰጥ ይህን የህግ አውጭነት ስልጣን ላልተመረጡ ግን ለተሾሙ ስራ አስፈፃሚዎች በውክልና እንዲያስተላልፉት አይደለም፡፡ ከዚህ ሀሳብ በተቃራኒ ስልጣን በውክልና ከተላለፈ ህዝቡ ድምፅ ሰጥቶ ባልመረጣቸው ስራ አስፈፃሚዎች እየተገዛ ነው፡፡ሁለተኛው የውክልና ህግ ንድፈ ሀሳባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ክፍፍል መርህ (separation of powers) የሚነሳ ሲሆን ዞሮ ዞሮ መሰረቱ የአስተዳደር በደል እንዲንሰራፋ ያደርጋል የሚል ነው፡፡ በስልጣን ክፍፍል መርህ መሰረት ህግ ማውጣት ለህግ አውጭው፤ ህግ መተርጐም ለፍርድ ሰጭው፤ ህግ ማስፈፀም ለአስፈፃሚ ተብሎ የእያንዳንዱ የመንግስት አካል ስልጣኑ ተመድቦና ተለይቶ ተሰጥቷል፡፡ አንድ የመንግስት አካል በተደራራቢነት ከአንድ በላይ ስልጣን የያዘ እንደሆነ ከራሱ በላይ ተቆጣጣሪ የሌለው ስልጣኑን እንዳሻው የሚጠቀም አምባገነን ይሆናል፡፡ ስለሆነም ስራ አስፈፃሚው ከተመደበለት ህግ የማስፈፀም ተግባር በተጨማሪ በደንብና መመሪያ ስም ህግ የሚያወጣ ከሆነ ሁለት የመንግስት ስልጣናትን ደርቦ ስለመያዙ ያም የስልጣን ክፍፍል መርህን መጣሱ ግልጽነቱ ጐልቶ የሚታይ ሀቅ ነው፡፡ከላይ በተጠቀሱት ሁለት ንድፈ ሀሳብ ተቃውሞዎች መሰረት በውክልና የሚወጣ ህግ አስተዳደራዊ አምባገነናዊነት፤ የአስተዳደር ብልሹነት እና በስልጣን አለአግባብ መገልገል እንዲሰራፋ ያደርጋል በሚል ከመስኩ ባለሙያዎች የሰላ ሂስና ትችት ሲገጥመው ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ እንግሊዝ አገር ውስጥ ሎርድ ሄዋርት የተባሉ የተከበሩ ዳኛና ምሁር በአገራቸው በየጊዜው በፍጥነት እያደገ የመጣውን የአስተዳደር መ/ቤቶች በውክልና ህግ የማውጣት ስልጣን ‘The New Despotism’ በሚለው መጽሐፋቸው እ.ኤ.አ. በ1931 ዓ.ም. ያቀረቡት ጠንካራ ተቃውሞ የእንግሊዝ ፓርላማ ስለጉዳዩ የሚያጠና አጣሪ እንዲሾምና ምርመራ እንዲያደርግ ምክንያት ሆኗል፡፡b ይሁን እንጂ ከምርመራው በኋላ የቀረበው የምርመራ ሪፖርት (Committee on Ministers’ Powers Report) የደረሰበት ድምዳሜ የውክልና ህግ እንግሊዝ ውስጥ በፍጥነት እያደገ መሆኑን ይህም በመሰረተ ሀሳብ ደረጃ ተቀባይነት እንደሌለው ካተተ በኋላ በተግባር ግን የግድ አስፈላጊና መቅረት የሌለበት አሰራር መሆኑን በአጽንኦት ገልጿል፡፡cከላይ የቀረቡት ንድፍ ንድፈ ሀሳባዊ ተቃውሞዎች አሳማኝ የመሆናቸውን ያህል እየተወሳሰበ ከመጣው የመንግስት አስተዳደር ጋር ተያይዘው የሚነሱ ተግባራዊ ምክንያቶች አስፈላጊነቱን አይቀሬና የበለጠ አሳማኝ አድርገውታል፡፡ የአስተዳደር መ/ቤቶች በህግ አውጭው በሚወጡት አዋጆች ላይ ብቻ ተንተርሰው ውጤታማ አስተዳደር ማስፈን አይቻላቸውም፡፡ በተለያዩ አገራት እንደታየው ህግ አውጭው ከሚያወጣቸው ህጐች በበለጠ የአስተዳደር መ/ቤቶች የሚያወጧቸው መመሪያዎች በፍጥነት እየበዙ መጥተዋል፡፡d በየጊዜው እያደገና እየተወሳሰበ የመጣው የመንግስት አስተዳደር ስራና የህግ አውጭው ለዚህ ስራ ውጤታማነት የሚያግዙ ህጐችን በአይነትና በጥራት ለማቅረብ አለመቻል በውክልና ስልጣን የሚወጣ ህግ አማራጭ ሳይሆን የግድ መሆኑን ያሳየናል፡፡ለዚህም ይመስላል ታዋቂው የአስተዳደር ህግ ምሁር ደብሊው ኤች. አር. ዌድ በውክልና የሚወጣ ህግን “መጥፎ ግን አስፈላጊ” (necessary evil) ሲል የሚገልፀው፡፡e ከህግ አውጭው በሚሰጥ ውክልና ህግ የማውጣት ስልጣንን በተግባር አስፈላጊ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የሚከተሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡የጊዜ እጥረትህግ አውጭው ስልጣኑን በከፊል ቆርሶ በውክልና ለማስተላፍ ከሚገደ`ድባቸው ምክንያቶች አንዱ ከራሱ ከህግ አውጭነቱ የሚመነጭ ችግር ነው፡፡ አንድን አዋጅ ለመደንገግ ከሚወስደው ረጅም ጊዜና ተፈጻሚ ከሚሆነው የጠበቀ የስነ-ስርዓት አካሄድ አንጻር ውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ህጐችን በብዛትና በጥራት ለማውጣት አስቸጋሪ ነው፡፡f የተወካዮች ም/ቤትን ያየን እንደሆነ ከሁለት ወራት የክረምት የእረፍት ጊዜ በኋላ በመካከል ለአንድ ወር ለእረፍት ሲበተን ጠቅላላ የስራ ጊዜው ከዘጠኝ ወራት አይበልጥም፡፡g ከዘጠኙ ወራት ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ተቀንሰው በሚቀሩት የስራ ቀናት ባሉት አጭር የስራ ሰዓታት ለአገሪቱ አስፈላጊ አዋጆችን ማውጣት አዳጋች ነው፡፡ የመስኩ ምሁራን እንደሚስማሙበት የአንድ አገር ፓርላማ ለተከታታይ 365 ቀናት ድፍን 24 ሰዓታት በስራ ላይ ቢቆይ እንኳን በብዛትና በጥራት ለአገሪቱ አስፈላጊ የሆኑ ህጐችን ማቅረብ ይሳነዋል፡፡hበተወሰኑ ዘርፎች የተወካዮች ምክር ቤት ያወጣቸው አዋጆች እና በውክልና የወጡ መመሪያዎች ቁጥር ብናነጻጽር ከጊዜ እጥረት ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር በተግባራዊ ምልከታ ለመመዘን ያስችለናል፡፡ ምክር ቤቱ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ ቀረጥና ታክስ በሚመለከት (ማሻሻያዎችን ጨምሮ) ያወጣቸው አዋጆች በቁጥር ከ25 አይበልጡም፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ እነዚህን ህጎች ለማስፈጸም በተለያየ ቅርጽና ስያሜ ተዋቅረው በነበሩትና በኋላም ከሐምሌ 2000 ዓ.ም. ጀምሮ ስልጣናቸውን አዋህዶ በተረከበው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንi በውክልና ስልጣኑ 129j መመሪያዎች ወጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዲሁ የባንክ፣ የመድን፣ የአነስተኛ ፋይናንስ እና የካፒታል ዕቃ ኪራይ ስራዎችን ለመቆጣጠር ከወጡ ወደ ሰባት የሚጠጉ አዋጆችና በሌሎች ልዩ ህጎች በተሰጠው ስልጣን ከ110 በላይ መመሪያዎችን አውጥቷል፡፡k ሌሎች የአስተዳደር መ/ቤቶች እያንዳንዳቸው በቁጥር ወደ 100 የሚጠጉ መመሪያዎች ባይኖራቸውም ከብዛታቸው አንጻር ጠቅላላ ድምሩ ከ1000 ያልፋል፡፡ በዚህ ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እስከ ጥር 2008 ዓ.ም. ድረስ ያወጣቸውን 371 ደንቦች ስንጨምርበት በውክልና ስልጣን የሚወጡ አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች ቁጥር ወደ ላይ በጣም ያሻቅባል፡፡የተወካዮች ምክር ቤት እስከ ነሀሴ 2008 ዓ.ም. ድረስ ካወጣቸው አዋጆች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በአጭር ጊዜ የሚወጡ ዓለም ዓቀፍና የሁለትዮሽ ስምምነቶችና የብድር ማፅደቂያ አዋጆች ናቸው፡፡ ስለሆነም ም/ቤቱ ሁሉንም ደንቦችና መመሪያዎች ራሱ ለመደንገግ ቢወስን በተግባር ሊወጣው አይችልም፡፡የእውቀት እጥረትየህዝብ ተመራጮች ለመመረጣቸው ምክንያት እውቀት ወይም ብቃት አንዱ መለኪያ ቢሆንም ዋናው መስፈርት ግን በህዝብ ዘንድ ያላቸው አመኔታና ተቀባይነት ነው፡፡ በጠቅላላ ጉዳዮች ጠቅላላ እውቀት ይኖራቸዋል ብለን ብንገምት እንኳን ከመንግስት አስተዳደር ውስብስብነት አንፃር ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ላይ የበለጠ እውቀትና ችሎታ ያለው በአስተዳደር መ/ቤቶች ዘንድ ነው፡፡l ስለሆነም ፓርላማው ትኩረቱን በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በማነጣጠር ዝርዝር የአፈፃፀም ስልት የሚጠይቁ ቴክኒካል ጉዳዮች በደንብና በመመሪያ እንዲወሰኑ ስልጣኑን በውክልና ማስተላለፍ የግድ ይለዋል፡፡m የእውቀት እጥረት መኖሩ ብቻ ሳይሆን የአስተዳደር መ/ቤቶች በተቋቋሙለት ዓላማ ስር ልዩና ብቁ የሰው ኃይል ማፍራታቸው ስልጣንን በውክልና ማስተላለፍ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ተመራጭም ያደርገዋል፡፡ተለዋዋጭ ሁኔታአንድ ህግ ፀድቆ ከወጣ በኃላ ወደፊት ለሚያጋጥሙ ችግሮች በሙሉ በቂ ምላሽ አይሰጥም፡፡ መሰረታዊው ችግር እልባት ቢያገኝ እንኳን ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚፈጠሩ የአፈጻጸም ችግሮች ይኖራሉ፡፡ የህግ አውጭው የህግ አወጣጥ ስነ-ስርዓት የጠበቀና ጊዜ የሚፈጅ ከመሆኑ አንጻር በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን ከተለዋዋጭ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች አንጻር በተከታታይ አዋጅ በማውጣት ምላሽ መስጠት አይታሰብም፡፡ በተቃራኒው አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስነ-ስርዓት እጅጉን የቀለለ እንደመሆኑ ችግሮችን እየተከታተሉ አግባብነት ያለው መፍትሔ ለመቀየስ ያስችላል፡፡n በሌላ አነጋገር ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተለዋዋጭ መፍትሔ ለመስጠት አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ፣ ነዋሪ ያልሆኑና ለጉብኝት የመጡ ሰዎች ወይም ሌላ ማንኛውም ሰው የውጭ ምንዛሪ የሚይዝበትንና ወይም በውጭ ምንዛሪ ክፍያ የሚፈጽምበትን ወይም የክፍያ ማዘዣዎችን የሚይዝበትንና የሚጠቀምበትን ሁኔታዎችና ገደቦች በመመሪያ እንዲወስን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡o እነዚህ ሁኔታዎችና ገደቦች በጊዜ ሂደት የሚለዋወጡ እንደመሆናቸው የተወካዮች ምክር ቤት በቅርበት እየተከታተለ በየጊዜው አዋጅ በማውጣት ቁጥጥር ለማድረግ የህግ አወጣጥ ስርዓቱ አይፈቅድለትም፡፡አስቸኳይ ሁኔታአስቸኳይ መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ ሲያጋጥም አዋጅ ለማውጣት ከሚያስፈልገው ረጅም ጊዜ አንጻር ፈጣን ምላሽ መስጠት አስቸጋሪ ነው፡፡ በተቃራኒው ደንብና መመሪያ በአንድ ሳምንት ምናልባትም ከዚያም ባነሰ ጊዜ ሊወጣ ይችላል፡፡ ስለሆነም ልዩና አስቸኳይ እርምጃ ለመውሰድ አስፈላጊ በሆነበት ሁኔታ ከፓርላማው ይልቅ ስራ አስፈፃሚው ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ በውክልና ህግ የማውጣት ስልጣን ሊኖረው ይገባል፡፡ከአስቸኳይነት ጋር ተያያዞ ምስጢራዊነት ሌላው ውክልናን አስፈላጊ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንደኛው ነው፡፡ የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝነቱ ባያጠያይቅም ከፊል በሆኑ ሁኔታዎች በአስቸኳይ ሊወሰዱ የታሰቡ እርምጃዎች ደንብና መመሪያው ከመፅናቱ በፊት ቀድመው ከታወቁ ሊሳካ የታሰበው ግብ ይሰናከላል፡፡ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በሚያስተዳድራቸው ቤቶች ላይ የተፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራት ስርዓት ለማስያዝ በሚል በመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ የወጣው መመሪያp ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ መመሪያው በሽንሸና ቤቱን ከተከራየው ግለሰብ የተከራዩ ሰዎች በራሳቸው ስም ከኤጀንሲው ጋር ውል እንዲገቡ ይፈቅዳል፡፡ ኤጀንሲው ሊወስደው ያሰበው እርምጃ ቀድሞ ቢታወቅ መመሪያው ሊያሳካ ያሰበው ግብ ይከሽፋል፡፡

Featured

ፈቃደ ስልጣን

ፈቃደ ስልጣን Discretion ወይም Discretionary Power ለሚለው ቃል ትክክለኛ ምትክ የአማርኛ ቃል ማግኘት ያዳግታል፡፡ በአማርኛ ‘ስልጣን’ ስንል በእንግሊዘኛው አራት የተለያየ መጠሪያ ካላቸው ቃላት መካከል አንደኛውን ወይም ሌላኛውን ማለታችን ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም ‘ስልጣን’ የሚለው የአማርኛ ቃል Power, Discretion, Jurisdiction ወይም Authority ለሚሉት የእንግሊዝኛ ቃላት ወካይ ነው፡፡ Discretion ቁርጥ ያለ የአማርኛ ፍቺ የለውም፡፡ ስለሆነም ወደ ትርጓሜ ከመሄዳችን በፊት ወካይ ቃል ልንፈልግለት ይገባል፡፡ ከይዘቱ አንጻር Discretion እና ‘አማራጭ ስልጣን’ እንደ አቻ ፍቺ ብንወስዳቸው ያስኬዳል፡፡ ምክንያቱም የዚህ ዓይነት ስልጣን ከተለያዩ ተግባራት መካከል አንዱን ወይም ሌላኛውን ለመፈጸም ምርጫ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ‘አማራጭ ስልጣን’ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ፈጽሞ አለመታወቁ ብቻ ሳይሆን Discretion ሰፊና የተለጠጠ የስልጣን ዓይነት የመሆኑን እውነታ ፍንትው አድርጎ አያሳይም፡፡አዲስ የአማርኛ ቃል መፍጠር አስቸጋሪ እንደመሆኑ ግልጋሎት ላይ ከዋሉ የተለመዱ ቃላት መካከል ተቀራራቢውን መምረጥ ግድ ይላል፡፡ በዚህ መሰረት discretion የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል በአግባቡ ሊገልጸው የሚችል የአማርኛ ቃል ‘የበዘፈቀደ ስልጣን’ ነው፡፡ በእርግጥ ‘በዘፈቀደ’ ሲባል የተለመደው ትርጉሙ አንዳችም ዓይነት ስርዓትና አካሄድ ያልተከተለ (arbitrary) ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አሉታዊ ጎኑን ብቻ ያጎላዋል፡፡ ይሁን እንጂ በጥሬ ትርጉሙ ‘በዘፈቀደ’ ማለት እንደፈቀደ፣ እንደወደደ፣ እንዳሻው ማለት ነው፡፡ discretionary power በእርግጥም ‘የእንደፈቀደ፣ የእንደወደደ፣ የእንዳሻው ስልጣን’ ነው፡፡ ከቋንቋ አጠቃቀም አንጻር በዘፈቀደ የሚለው ቃል ተመራጭ የሚያደርገው ከገላጭነቱ አንጻር ብቻ ሳይሆን discretionary Power አዎንታዊ ጥቅሙን እና አሉታዊ ጉዳቱን አንድ ላይ ጠቅልሎ የሚይዝ በመሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ‘በዘፈቀደ’ በበጎ ጎኑ በመግባባያነት ውሎ ስላማያውቅ እዚህ ላይ መጠቀሙ አንባቢን ማደናገሩ አይቀርም፡፡ ስለሆነም የውሳኔ ሰጭውን የተለጠጠ ፈቃድ እና ምርጫ በሚያንጸባርቅ መልኩ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ‘ፈቃደ ስልጣን’ የእንግሊዝኛውን discretion ወይም discretionary power እንዲወክል ተደርጓል፡፡በቀጣይ ወደ ጽንሰ ሀሳቡ ዳሰሳ እናመራለን፡፡ ለመሆኑ ፈቃደ ስልጣን (discretion) ሲባል ምን ማለት ነው? ልኩና ገደቡስ የት ላይ ነው? በመደበኛነት ከሚታወቀው ስልጣን (Power) የሚለየውስ ምንድነው?ፈቃደ ስልጣንን በጥልቀት በማጥናት በመስኩ ትልቅ አስዋጽኦ ካበረከቱ የአስተዳደር ህግ ሊቆች መካከል ስሙ በአንደኛነት የሚነሳለት ኬንዝ ከልፕ ዴቪስ (Kenneth Culp Davis) ፈቃደ ስልጣንን እንደሚከተለው ይገልፀዋል፡፡A public officer has discretion whenever the effective limits of his power leave him free to make a choice among possible causes of action and inaction.aአንድ ባለስልጣን ፈቃደ ስልጣን አለው የሚባለው የስልጣኑ ገደብ ማድረግ ከሚችላቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል አንዱን ወይም ሌላኛውን የመምረጥ ነፃነት ሲኖረው ነው፡፡ስለሆነም ፈቃደ ስልጣን ሲባል ውሳኔ ሰጪው አንድ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያለውን የምርጫ ወይም የፈቃድ ደረጃ ያመለክታል፡፡ በሌላ አነጋገር አንድን ድርጊት ለመፈፀም ወይም ላለመፈፀም ለውሳኔ ሰጪው የተሰጠው የመለጠጥ ነፃነት ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ በማናቸውም ከህግ በሚመነጭ ስልጣን (power) ውስጥ ደረጃው ቢለያይም የተወሰነ የመለጠጥ ነፃነት ይኖራል፡፡ ሆኖም የፈቃደ ስልጣንን ባህርያት ከመደበኛው በስነ-ስርዓትና በቅድመ ሁኔታ ከታጠረ ስልጣን (power) ጋር ብናነፃፅረው የተወሰነ ልዩነት እናያለን፡፡ለንጽጽር እንዲረዳን በመጀመሪያ ፈቃደ ስልጣን በአንዳንድ ህጎች ላይ የተሰጠበትን መንገድ እናያለን፤በብሔራዊ ዕጽዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ የሚመደብ የዘር ኢንስፔክተር አንድ ዘር የተደነገገ ዘር (የዕፅዋት ዘር አዋጅ ቁ 206/1992 ድንጋጌዎች ተፈጻሚ የሚሆኑበት) መሆኑን እና የጥራት ደረጃውን ለመወሰን እንዲሁም ደግሞ በኤጀንሲው በተሰጠው ስልጣን መሰረት አስፈላጊ ነው ብሎ ላመነባቸው ለሌሎች ምክንያቶች የዘር ወይም የተክል ናሙናዎችን ለመውሰድ ይችላል፡፡b (ሰረዝ የተጨመረ)በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በግብይት ፈጻሚነት ዕውቅና ለማግኘት የሚፈልግ ሰው ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ማመልከቻ ማስገባት ያለበት ሲሆን ማመልከቻው በባለስልጣኑ መመሪያ መሰረት በተዘጋጀው ቅጽና የአቀራረብ ስርዓት መሰረት ባለስልጣኑ አስፈላጊ ናቸው የሚላቸውን መረጃዎችና ፍሬ ነገሮች አካቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡c (ሰረዝ የተጨመረ)የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የመስመር ዝርጋታ፤ ጥገና ወይም ተዛማጅ ተግባራትን ለማከናወን ወደ ማንኛውም መሬት መግባት እንዲሁም በመስመር ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ዛፍ ካለ መቁረጥ የሚችል ሲሆን የመሬቱ ባለይዞታ ተቃውሞ ካለው ለኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኤጀንሲ አቤቱታ የማቅረብ ዕድል ተሰጥቶታል፡፡ ኤጀንሲው ለድርጅቱ እና ለባለይዞታው የመሰማት ዕድል በመስጠት ተቃውሞውን ከመረመረ በኋላ ተቃውሞውን ለመቀበል ወይም የታቀደው ተግባር ያለአንዳች ገደብ ወይም ተገቢ መስሎ የታየውን ገደብ በማድረግ እንዲከናወን ሊፈቅድ ይችላል፡፡d (ሰረዝ የተጨመረ)የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ቦርድ በማናቸውም ፍርድ ቤቶች በሚሰራባቸው የሥነ-ሥርዓትና የመረጃ አቀራረብ ደንቦች ሳይወሰን የተሻለ መስሎ በሚታየው ማናቸውም ዘዴ ሊጠቀም ይችላል፡፡e (ሰረዝ የተጨመረ)‘አስፈላጊ ነው ብሎ ላመነባቸው’፣ ‘አስፈላጊ ናቸው የሚላቸውን’፣ ‘ተገቢ መስሎ የታየውን’ በሚል አገላለጽ የሚሰጡ ስልጣናት ለአስተዳደር ህግ የራስ ምታት ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የስልጣን አሰጣጥ ከዜጐች መብትና ነፃነት አንጻር አደጋው የከፋ፣ አስጊና አሳሳቢ ስለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በአግባቡ ካልተገራ በስተቀር ፈቃደ ስልጣን ወደ ሙስና እና ብልሹ አስተዳደር የማምራት አዝማሚያው ከፍ ያለ ነው፡፡አደጋውና ስጋቱ ቢኖርም በህዝብ አስተዳደር ውስጥ ፈቃደ ስልጣን አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል፡፡ ሁልጊዜ ስልጣንን እንደ ቁና እየሰፈሩ በልክ መስጠት በውጤታማ አስተዳደር ላይ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ አስተዳደራዊ ውሳኔ ከመወሰዱ በፊት ሊሟሉ የሚገባቸውን ስነ-ስርዓቶችና ቅድመ ሁኔታዎች በማስቀመጥ በከፊልም ቢሆን የስልጣን አለአግባብ መገልገልን በህግ የቁጥጥር ማእቀፍ ስር ማድረግ ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ህግ አውጭው ስፋትና ጥልቀቱን በውል ለይቶ ያላወቀውን ችግር በአግባቡ ለመፍታት በተለዋዋጭ ችግሮች ልክ የሚለጠጥ ፈቃደ ስልጣን ያስፈልጋል፡፡ በህጉ ላይ በዝርዝር ሊዳሰሱ የማይችሉ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጊዜና ወቅቱን የጠበቀ አግባብ ያለው የእርምት እርምጃ ሊወሰድባቸው የሚችለው ውሳኔ ሰጪው አካል በሚለጠጡት ሁኔታዎች ልክ ተለጣጭ ስልጣን ሲሰጠው ነው፡፡

Featured

ህገ መንግስታዊ ገደብ

ህገ መንግስታዊ ገደብ በውክልና ህግ የማውጣት ስልጣን የአስፈላጊነቱ አጥጋቢ ምክንያት ተግባራዊ ችግሮች ቢሆኑም የመንግስት አስተዳደርን ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ ረገድ ራሱን የቻለ የጐላ ጥቅም አለው፡፡ በእርግጥ የስልጣን አምባገነንነትን ሊያስከትል ከመቻሉ የተነሳ የራሱ አደጋዎችም አሉት፡፡ አደጋውና አላስፈላጊ ጐኑ ሊወገድ የሚችለው ልኩ ተለይቶ በታወቀ ገደብ ውሰጥ ተግባር ላይ የዋለ እንደሆነ ነው፡፡ ውክልናው ግልጽ፣ የማያሻማ፣ ጠባብና ገደብ የተሰመረለት ሊሆን ይገባዋል፡፡የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ህግ የማውጣት ስልጣን ለተወካዮች ም/ቤት እንደተሰጠ በግልፅ ይደነግጋል፡፡a ይህ ስልጣን በውክልና እንዲተላለፍ የሚፈቅድ ግልጽ ድንጋጌ ግን አልሰፈረም፡፡ ስልጣኑን በውክልና እንዲያስተላልፍ የሚፈቅድለት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ባይኖርም የተለያዩ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ውክልና ቢያንስ በተዘዋዋሪ የተከለከለ እንዳልሆነ ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል፡፡ በተለይ አግባብነት ያለው የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 13 የሚኒስትሮች ም/ቤት የተወካዮች ም/ቤት በሚሰጠው ስልጣን መሰረት ደንብ የማውጣት ስልጣን እንዳለው ይደነግጋል፡፡ ከዚህ አንጻር የተጠቀሰው ድንጋጌ ህግ የማውጣት ስልጣንን በውክልና ማስተላለፍ ኢ- ህገ መንግስታዊ ስላለመሆኑ በቂ መከራከሪያ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡ለአስተዳደር ህግ አስጨናቂው ጥያቄ ህገ መንግስቱ የተወካዮች ም/ቤት በውክልና ስልጣኑን እንዲያስተላልፍ የመፍቀዱ ነገር ሳይሆን በውክልና ሊተላለፍ የሚችለው ስልጣን ወሰንና ገደቡ የትላይ ነው? የሚለው ነው፡፡ ህግ አውጭው በህዝብ የተመረጠው ህግ ለማውጣት ነው፡፡ ስለሆነም የህግ አውጭነት ስልጣኑን ያለገደብ ወይም ሙሉ በሙሉ ለአስፈፃሚው አካል ማስተላለፍ የለበትም፡፡

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሠራተኞች

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሠራተኞች አስተዳዳርፍትህ የማግኘት መብትን የሚደነግገው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 37/1/ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው፡፡የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሰራተኞች አስተዳደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 155/2000 በልዩ ሁኔታ ሰራተኞችን ማሰናበትን በተመለከተ በአንቀጽ 37 እንደሚከተለው ደንግጓል፡፡1) በዚህ ደንብ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው ቢኖርም ዋና ዳይሬክተሩ በሙስና የተጠረጠረንና እምነት ያጣበትን ሰራተኛ መደበኛውን የዲስፕሊን አፈፃፀም ስርዓት ሳይከተል ከስራ ማሰናበት ይችላል፡፡2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ በየትኛውም የፍርድ አካል ውሳኔ ወደ ስራ መመለስ አይችልም፡፡የህገ መንግስቱና የደንብ ቁ. 155/2000 ድንጋጌዎች በስም (አንቀጽ ቁጥር) ይመሳሰላሉ፡፡ በተግባር ግን ተጻራሪ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው መብት ያናጽፋል፤ ሁለተኛው ይነፍጋል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህገ መንግስቱን የማክበርና የማስከበር ግዴታ ከተጣለባቸው አካላት መካከል አንደኛው ነው፡፡ በዚህ ግዴታው የህግ አውጭነት ስልጣኑ ምንጭ የሆነው ህግ ያሰመረለትን ወሰን ሊያከብር ይገባል፡፡ ምክር ቤቱ ደንብ ቁ. 155/2000 ለማውጣት ህግ እንደፈቀደለት የሚጠቅሰው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ አዋጅ ቁ. 587/2000 አንቀጽ 19/1/ ለ ድንጋጌ ነው፡፡ ይዘቱ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡[የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን] ሠራተኞች አስተዳደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይመራል፡፡በስልጣን ምንጭነት የተጠቀሰው ህግ ም/ቤቱ የሠራተኞች አስተዳደርን በተመለከተ ደንብ እንዲያወጣ ይፈቅድለታል፡፡ ይሁን እንጂ ሠራተኞች በጥርጣሬ እንዲሰናበቱና በየትኛውም የፍርድ አካል መብቸውን እንዳይጠይቁ የሚከለክል ኢ-ህገ መንግስታዊ ደንብ እንዲያወጣ ስልጣን አልሰጠውም፡፡

MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE HOME

Definitions of the Constitution

CRIMINAL PROCEDURE RULES

AND DISCIPLINE PROCEDURES

CRIMINAL PROCEDURE CODES

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስርዓትስነ-

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስርዓትስነ-

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስርዓትስነ-ስርዓት ዋነኛው አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን መቆጣጠሪያ መንገድ ሲሆን የበዘፈቀደ አሰራርን በማስወገድ ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡ ዝርዝር የአስተዳደራዊ ድንጋጌ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በውክልና የተሰጠ ስልጣን በአግባቡ ተግባር ላይ ስለመዋሉ አንዱ መለኪያ መስፈርት ነው፡፡በአንዳንድ አገራት አስተዳደራዊ ድንጋጌ የሚወጣበት ወጥ የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ደንብ (Administrative procedure code) ራሱን ችሎ በተለይ ይደነገጋል፡፡ ወጥ ስነ-ስርዓት በሌለበት ሁኔታ ግን የውክልና ስልጣኑን የሚሰጠው ህግ የአስተዳደር መ/ቤቱ መከተል ያለበትን አነስተኛ የስነ-ስርዓት አካሄድ ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ በአገራችን በሚኒስትሮች ም/ቤት ደረጃ ሆነ በአስተዳደር መ/ቤቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን አስገዳጅና ወጥ የስነ-ስርዓት ደንብ ካለመኖሩም በላይ የውክልናው ምንጭ የሆነው አዋጅ ዝርዝር የስነ-ስርዓት ድንጋጌዎችን አያስቀምጥም፡፡ በዚህ የተነሳ አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች ውጤታማ አስተዳደር በማስፈን ረገድ ያላቸውን ሚና ከማሳነሱም በላይ ለህገ-ወጥ አሠራር፣ ሙስና እና አስተዳደራዊ ብልሹነት መንሰራፋት አይነተኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ከሌሎች አገራት ተሞክሮ እንደምንረዳው ልዩ ሁኔታዎች እንደ ተጠበቁ ሆነው በውክልና ህግ የሚያወጣ አካል የሚከተሉትን የስነ-ስርዓት ደንቦች መከተል ይጠበቅበታል፡፡ እነዚህም ስነ-ስርዓቶች ማስታወቂያና መረጃ መስጠት፣ ምክክር (የህዝብ ተሳትፎ)፣ ክለሳ እንዲሁም ህትመት በሚል በአራት ዋና ዋና ንዑስ ስርዓቶች ልንከፍላቸው እንችላለን፡፡እነዚህ ንዑስ የስነ-ስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ጥሩ ሊባል የሚችል አስተዳደራዊ ደንብ ወይም መመሪያ ከማርቀቅ ሂደት እንደሚጀምር ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ሲረቀቅ ያላማረ ሲጸድቅም አያምርም፡፡ ስለሆነም ደንቡ ወይም መመሪያው ግልጽ፣ በቀላሉ የሚገባ፣ የማያደናግር ይሆን ዘንድ በማርቀቅ ሂደቱ ላይ የህግ ባለሙያ ተሳትፎ ተመራጭነት አለው፡፡aማስታወቂያ እና መረጃ መስጠትየህዝብ ተሳትፎ ለአስተዳደራዊ ድንጋጌው ተዓማኒነትና ተቀባይነት ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ መሰረት ሀሳብ በተግባር የሚተረጎመው ግልፅ የሆነ የሕዝብ ተሳትፎ ማስፈፀሚያ ስርዓት ሲኖር ነው፡፡ በዚህ ረገድ አስተዳደራዊ ደንቡ ወይም መመሪያው ከመታተሙ በፊት የሚመለከተው የህብረተሰብ ክፍል ሀሳብ፣ ጥቆማ፣ አስተያየት፣ ትችትና ሂስ ለመስጠት እንዲያስችለው ረቂቁን በቀላሉ ማግኘት የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡ለምሳሌ በአሜሪካ የካሊፎርኒያ ግዛት በውክልና ህግ የማውጣት ስነ-ስርዓት ብንወስድ የሚመከለተው የአስተዳደር መ/ቤት መመሪያ ለማውጣት ሲያቅድ አስቀድሞ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ጋዜጣ (state register) ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ረቂቁ መመሪያ በሙሉ ወይም በከፊል ከማስታወቂያው ጋር የሚወጣ ሲሆን በከፊል ከታተመ የረቂቁ ሙሉ ቅጂ ስለሚገኝበት አድራሻና ሁኔታ በጋዜጣው ላይ መግለጫ ይሰጣል፡፡ ስለሆነም አስተያየት ማቅረብ የሚፈልግ ወገን መመሪያ በሚያወጣው የአስተዳደር መ/ቤት በቀጥታ በአድራሻው በመሄድ የረቂቁን ቅጂ በነጻ ወይም በአነስተኛ ክፍያ ማግኘት ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከኢንተርኔት ድረ-ገጽ ላይ በቀላሉ ይገኛል፡፡bማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ለ45 ቀናት መቆየት ያለበት ሲሆን ዓላማውም በጉዳዩ ጥቅም ያላቸው ወገኖች አስተያየት፣ ጥቆማና ሂስ ለማቅረብ በቂ ጊዜ እንዲያገኙ ነው፡፡ ሀሳብ መስጠት የፈለገ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስተያየቱን በጽሁፍ፣ በፋክስ፣ በኢ-ሜይል ወይም በሌላ በሚያመቸው መገናኛ ዘዴ መላክ ይችላል፡፡በካሊፎርኒያ ሆነ በሌሎች ግዛቶች ያለው የአስተዳደራዊ ድንጋጌ አወጣጥ ስርዓት ከሞላ ጎደል እ.ኤ.አ. በ1946 ዓ.ም. በፌደራል መንግስት ደረጃ ከወጣው የአስዳደር ስነ ስርዓት ደንብ (Administrative Procedure Act, 1946) ከሚደነግጋቸው ቅድመ ሁኔታዎች ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡ በዚህ ህግ መሰረት የአስተዳራዊ ድንጋጌ (በህጉ አነጋገር ‘Rule’) አወጣጥ ስርዓቱ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ በሚል ለሁለት (እ.ኤ.አ በ1990 ዓ.ም. የህግ ዕውቅና ያገኘውን Negotiated Rulemaking ሳይጨምር) ተከፍሏል፡፡cመደበኛው ስርዓት እንደ ፍርድ ቤት ክርክር ዓይነት የጉዳዩ መሰማት የሚካሄድበት ሲሆን የሚመለከታቸው ወገኖች አስተያየት ከመስጠት ባለፈ የኤጀንሲውን አቋም ለማስተባበል ተቃራኒ ክርክር እና ማስረጃ ማቅረብ ይፈቀድላቸዋል፡፡d በአሜሪካ የፌደራል መ/ቤቶች በስፋት የሚከተሉትና እንዲከተሉትም የሚገደዱት ኢ-መደበኛውን ስርዓት ሲሆን መሟላት ያላባቸው አነስተኛ ቅድመ ሁኔታዎች ማስታወቂያ፣ አስተያትና ህትመት ናቸው፡፡ የአስተዳደራዊ ድንጋጌ (Rule) አወጣጥ ስርዓቱ ፌደራል ሬጅስተር በሚባለው ዕለታዊ የመንግስት ጋዜጣ ይፋ ማስታወቂያ በማውጣት ይጀመራል፡፡e ማስታወቂያው የሚከተሉትን መግለጫዎች መያዝ ይኖርበታል፡፡ሊወጣ የታቀደው አስተዳደራዊ ድንጋጌ የሚገኝበትን ቦታ፣ ጊዜ እና አጠቀላይ ባህርያቱንስልጣን የሰጠው አዋጅና ለድንጋጌው መውጣት መነሻ የሆነውን የህግ ምክንያትሊወጣ ስለታሰበው ድንጋጌ ይዘት እና በውስጡ የተካተቱ ጭብጦች አስመልክቶ አጠቃላይ መግለጫበአገራችን 1993 ዓ.ም. በተዘጋጀው ረቂቅ የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግf መሰረት ደንብ ማውጣት የሚፈልግ የአስተዳደር መ/ቤት ከ30 ቀናት በፊት የሚከተሉትን ፍሬ ነገሮች የያዘ ማስታወቂያ በጋዜጣg ማውጣት አለበት፡፡ስለ ረቂቅ ደንቡ ዓላማ አጭር ማብራሪያየደንቡ ረቂቅ የተፈቀደበት ሕጋዊ ስልጣንየደንቡ ረቂቅ ሰነድየደንቡ ረቂቅ ላይ ሰዎች የት፣ መቼና እንዴት አስተያየታቸውን እንደሚያቀርቡናየደንቡ ረቂቅ ላይ ስለሚሰጥ የቃል አስተያየት የማቅረብ ስርዓት በሚመለከት የት፣ መቼና እንዴት እንደሚካሄድ መጠየቅ እንደሚችሉ የሚገልጽ መረጃበ2001 ዓ.ም. ድጋሚ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይም እነዚህን አምስት መግለጫዎች የያዘ ማስታወቂያ በጋዜጣ ወይም በሌላ መገናኛ ብዙኃን ሊነገር እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡ የቃል አስተያየት (hearing) በአሜሪካ የመደበኛው ስርዓት ቅድመ ሁኔታ ሲሆን ተፈጻሚነቱ ተቋሙ ይህን ስርዓት እንዲከተል ህግ አውጭው በልዩ ህግ በግልጽ ባመለከታቸው ውስን ሁኔታዎች የተገደበ ነው፡፡ የአገራችን አርቃቂዎች ባይገለጥላቸውም አሜሪካኖች ይህን አካሄድ የመረጡበት ምክንያት ግልፅ ነው፡፡ የየትኛውም አገር አስተዳደር ውጤታማነት እና ቅልጥፍና ተቀዳሚ እሴቶቹ ናቸው፡፡ አንድ መመሪያ ለማውጣት እንደ ፍርድ ቤት ዓይነት ሙግት እየተደረገ፣ ደጋፊና የሚያስተባብል ማስረጃ እየቀረበ፣ የቃል ክርክር እየተሰማ በአጠቃላይ ከፍተኛ ወጪና ጊዜ በሚጠይቅ ሂደት ማለፍ አስገዳጅ ከሆነ አስተዳደር ይንዛዛል እንጂ አይቀላጠፍም፡፡ከላይ ከተዘረዘሩት የማስታወቂያ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በመጨረሻ ላይ የሚገኘው የቃል አስተያይት አቀራረብ ስርዓት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንደምታቸው ግዙፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ መወሰን ይኖርበታል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ለመለየት ቋሚ መለኪያ ማበጀት ብዙም አይጠቅምም፡፡ ምክንያቱም በጊዜና በሁኔታ ይለዋወጣሉ፡፡ ዛሬ ላይ ሲመዘን ክብደት የሚሰጠው ጉዳይ በጊዜ ሂደት ፋይዳው ሊያንስ ይችላል፡፡ ስለሆነም አሜሪካኖቹ እንደተከተሉት አማራጭ ህግ አውጭው በየጊዜው በሚያወጣቸው አዋጆች ቢወሰኑ ይሻላል፡፡ በሌላ አነጋገር የቃል አስተያየት የማቅረብ ስርዓት አስገዳጅነት የተወካዮች ም/ቤት በየጊዜው በሚያወጣቸው አዋጆች በግልፅ ሲደነገግ ብቻ ተፈጻሚ ሊሆን ይገባል፡፡ማማከር እና ማሳተፍ‘ምክክር’ የሚለው ቃል ከህዝብ አስተያየት መሰብሰብንና በአስተዳደራዊ ድንጋጌ አወጣጥ ሂደት እንደ ግብዓት መጠቀምን ያመለክታል፡፡ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ሀሳብ ከመቀበል በተጨማሪ ምክክር አልፎ አልፎ በተወሰኑ ሁኔታዎች በቀጥታ የሚደረግ ውይይት ወይም ስብስባ ሊያካትት ይችላል፡፡ በጉዳዩ ጥቅም ያላቸው ወገኖች ተሳትፎ ሕዝባዊ ተቀባይነትና አመኔታን ያረጋግጣል፡፡ ተግባራዊ አፈጻጸሙንም ምቹ ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ዜጐች በቅድሚያ አውቀውት እንቅስቃሴያቸውን በደንቡና መመሪያው መሰረት እንዲያስተካክሉ ይረዳቸዋል፡፡ምክክር ትርጉም የሚኖረው እውነተኛና በተግባር ለውጥ የሚያመጣ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ በካሊፎርኒያ ግዛት መመሪያውን የሚያወጣው የአስተዳደር መ/ቤት በህዝብ ከቀረቡ አስተያየቶችና ጥቆማዎች መካከል ያመነባቸውና የተቀበላቸው ካሉ በረቂቁ ላይ ማካተትና የማይቀበል ከሆነም ያልተቀበለበትን ምክንያት በመግለጽ ለሁለቱም መግለጫ (statement of reasons) ማቅረብ አለበት፡፡ተጠያቂነት እና የክለሳ ስርዓትበውክልና የሚወጣ ደንብ ወይም መመሪያ በህግ አውጭው ከተሰመረለት ስልጣን በላይ አለማለፉን ማረጋገጥ ዋነኛው የአስተዳደር ህግ ዓላማ ነው፡፡ ዓላማውን ለመተግበር የስልጣን ወሰን ወይም ገደብ የሚቆጣጠር አካል ሊኖር ያስፈልጋል፡፡ በእንግሊዝ ይህ የማጣራት ወይም የክለሳ ሂደት የሚከናወነው በዋነኛነት በራሱ በፓርላማ ሲሆን በአሜሪካ በተለይ በካሊፎርኒያ ግዛት በህግ የተቋቋመና ራሱን የቻለ የአስተዳደር ህግ ጽህፈት ቤት (Administraive Law office) ተብሎ በሚጠራ ተቋም አማካይነት ቁጥጥር ይደረጋል፡፡ በእንግሊዝ የመመሪያውን ህጋዊነት የማጣራት ሂደትና ስነ-ስርዓት ብዙውን ጊዜ ውክልና በሰጠው አዋጅ ላይ ይደነገጋል፡፡ ይህ ስነ-ስርዓት የማንጠፍ ስነ-ስርዓት (Laying procedure) ተብሎ ሲጠራ ውክልና ተቀባዩ አካል አስተዳደራዊ ድንጋጌውን ለፓርላማው የማቅረብ (በፓርላማ ፊት የማንጠፍ ወይም የመዘርጋት (laying before parlament) ወይም (laying before the table) ቅድመ ሁኔታን ያሰቀምጣል፡በዚህ ስነ-ስርዓት ፓርላማው በሚያደረገው ፍተሻና ምርመራ መሰረት ድንጋጌው ከስልጣን በላይ አለመሆኑና በአግባቡ ስለመውጣቱ ይጣራል፡፡ የማንጠፍ ስነ-ስርዓቱ የተለያዩ ቅርጽና መልክ ይኖረዋል፡፡ ነፃ የማንጠፍ ስነ-ስርዓት (Bare laying procedure) ድንጋጌው ተፈፃሚነት ከማግኘቱ በፊት ትክክለኛ ቅጂው ለፓርላማው እንዲቀርብ ያስገድዳል፡፡h ዋና ዓላማው ፓርላማው የድንጋጌውን ይዘት እንዲያየው ከማድረግ አይዘልም፡፡ ስለሆነም ለፓርላማ ከቀረበበት ቀን አንስቶ ወዲያውኑ ውጤት ይኖረዋል፡፡አሉታዊ የማንጠፍ ስርዓት (Negative resolution procedure) ከሆነ ደግሞ ድንጋጌው ለፓርላማ ከቀረበ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ጥያቄ ከቀረበበትና ግድፈት ከተገኘበት ይሰረዛል ፡፡ ሆኖም ከመሰረዙ በፊት በድንጋጌው መሰረት የተወሰዱ እርምጃዎች እንደጸኑ ይቆያሉ፡፡ ካልተሰረዘ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ይሁንታ አግኝቷል ማለት ነው፡፡i ከዚህ በተቃራኒ ስርዓቱ አዎንታዊ የማንጠፍ ስርዓት (positive resolution procedure) በሚሆንበት ጊዜ ለፓርላማ ቀርቦ መፅደቅ ይኖርበታል፡፡j የማንጠፍ ስርዓት መከተል ያለበት አስተዳደራዊ ድንጋጌ ስርዓቱን ባልተከተለ መንገድ የወጣ እንደሆነ ዋጋ አልባ (void) እንደሆነ ይቆጠራል፡፡በአገራችን ይህን መሰሉ ሆነ ሌላ ዓይነት የክለሳ ስርዓት አልተለመደም፡፡ ከስልጣን በላይ የሆኑ ደንብና መመሪያዎች ሲወጡ ህግ አውጭው የሚቆጣጠርበት መንገድ ባለመኖሩ የሚኒስተሮች ም/ቤትና የአስተዳደር መ/ቤቶች ልጓም አልባ ለመሆን ብሎም በዘፈቀደ ህግ ለመደንገግ አጋጣሚ ያገኛሉ፡፡ ይህ ያልተገራ ስልጣን የዜጐች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፀር ሲሆን ህገ መንግስታዊ ዋስትናን ያሳጣል፡፡በካሊፎርኒያ በውክልና የሚወጣ ህግ ውጤት ኖሮት ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት የተወሰኑ መመዘኛዎች ማሟላት አለበት፡፡ መመዘኛዎቹ መሟላታቸውን የአስተዳደር ህግ ጽህፈት ቤት (Administraive Law Office) የተባለ በህግ የተቋቋመ አካል ያረጋግጣል፡፡ እያንዳንዱ መ/ቤት የሚያወጣውን አስተዳደራዊ ድንጋጌ ረቂቅ ለክለሳ ለዚህ ጽህፈት ቤት በቅድሚያ መላክ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ አንጻር ከእንግሊዝ የማንጠፍ ስነ-ስርዓት ጋር በከፊል ይመሳሰላል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ድንጋጌውን ሲከልስ የሚከተሉትን መመዘኛዎች መሰረት በማድረግ ነው፡፡ስልጣን (Authority)፤ የአስተዳደር መ/ቤቱ ድንጋጌውን እንዲያወጣ ከህግ አውጭው በእርግጥ ውክልና የተሰጠው መሆኑማጣቀስ (Reference)፤ የአስተዳደር መ/ቤቱ በሚያወጣው ድንጋጌ ላይ የሚያስፈጽመው ህግ እና ስልጣን የሰጠውን ህግ አንቀጽ መጥቀሱ (ማመልከቱ)ወጥነት (Consistencey)፤ ድንጋጌው ስልጣን ከሰጠው ወይም ከሌላ ህግ ጋር የተስማማ ወይም የማይቃረንና የማይጋጭ መሆኑግልፅነት (Clarity)፤ የድንጋጌው ትርጉም ግልጽና በቀላሉ ለመረዳት የሚቻል መሆኑአለመደጋገም (Non- duplication)፤ ድንጋጌው ስልጣን የሰጠውን ህግ ድንጋጌዎች መድገም የለበትም፡፡ የህጉ ይዘት በከፊል ወይም በሙሉ በድጋሚ በድንጋጌው ላይ ከሰፈረ መመዘኛው አልተሟላም፡፡ህትመት‘ህትመት’ የሚለው ቃል በአፍ የሚደነገግ መመሪያ እንደሌለ ያመለክታል፡፡ ‘የህግ መታተም’ ሲባል አዋጅ፣ ደንብ ወይም መመሪያ ለህዝብ በቀላሉ ሊደርስ በሚችል ወጥ የህትመት ውጤት ላይ ታትሞ ለህዝብ ማሰራጨት ማለት ነው፡፡ ህግ በጽሑፍ ላይ ሰፍሮ መውጣቱ ብቻ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ቁም ነገሩ ታትሞ መውጣቱ ሳይሆን ህትመቱ ይፋ መደረጉና በቀላሉ ለህዝቡ የሚደርስ መሆኑ ነው፡፡ ዜጎች ላልታተመና ይፋ ላልሆነ ብሎም በቀላሉ ለማይገኝ ህግ ሊገዙ አይችሉም፡፡ ድብቅ ህግ ህጉን ካወጣው አካል በስተቀር አውቆት የሚያከብረው አይኖርም፡፡በእንግሊዝ ውስጥ በብላክፑል ኮርፖሬሽን እና ሎከር (Blackpool Corporation Vs. Locker) መካከል በነበረው ክርክር ላይ በተሰጠ ውሳኔ የህትመት አስፈላጊነት እንዲህ ተገልጾ ነበር፡፡kህግን አለማወቅ ይቅርታ አያሰጥም የሚለው መርህ በእንግሊዝ ዲሞክራሲ የህግ የበላይነት የቆመበትን መሪ ሀሳብ ይወክላል፡፡ ነገር ግን የዚህ መርህ የትክክለኛነቱ መሰረት ሁሉም ህጐች በቀላሉ ለህዝቡ እንደሚደርሱ ግምት በመውሰድ ነው፡፡በአሜሪካ በእያንዳንዱ የፌደራል መንግስት የአስተዳደር መ/ቤት የሚወጣ አስተዳደራዊ ድንጋጌ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ፌደራል ሬጅስተር (Federal Regiser) ተብሎ በሚጠራ ወጥና መደበኛ ጋዜጣ ላይ መታተም አለበት፡፡ እያንዳንዱ መመሪያ በጋዜጣው ላይ ሲታተም የራሱ መለያ ቁጥር ስለሚሰጠው ፈልጐ ለማግኘት በጣም ቀላል ያደርገዋል፡፡ መመሪያውን ማግኘት የሚፈልግ ሰው ከመ/ቤቱ ወይም ከጋዜጣው ድረ-ገጽ ላይ በቀላሉ በነጻ ማንበብና መቅዳት ይችላል፡፡ በተጨማሪ በአካል ሄዶ ጋዜጣውን በአነስተኛ ክፍያ መግዛት ሌላው አማራጭ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1946 ዓ.ም. በወጣው የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ህግ (Administrative Procedure Act) መሰረት ማንኛውም መመሪያ ተፈፃሚነት የሚኖረው በፌደራል ሬጅስተር ከታተመ ከ30 ቀናት በኃላ ነው፡፡ በእነዚህ 30 ቀናት ውስጥ ማንኛውም ሰው መመሪያውን ለማግኘትና ይዘቱን ለመረዳት በቂ ጊዜ ያገኛል፡፡lበተመሳሳይ ወቅት (እ.ኤ.አ. በ1946 ዓ.ም.) በእንግሊዝ የወጣው ህግ (statutory instrumnets act) ከተወሰኑ አስተዳራዊ ድንጋጌዎች በስተቀር ከሞላ ጎደል ሁሉም ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት በይፋ እንዲታተሙና ለህዝብ እንዲሰራጩ ያስገድዳል፡፡m ህጉ በማያካትታቸው የአስተዳደራዊ ድንጋጌ ዓይነቶች ህትመት ቅድመ ሁኔታ ባይሆንም አብዛኛዎቹ የአስተዳደር መ/ቤቶች በራሳቸው ተነሳሽነት እንዲታተሙ ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም በልዩ ህግ ላይ ህትመት እንደ ቅድመ ሁኔታ ከተቀመጠ አስገዳጅ ነው፡፡ ድንጋጌው በይፋ ካልታተመ ውጤት ወይም ዋጋ አይኖረውም፡፡በህንድ ኦፊሴሊያዊ በሆነ ጋዜጣ እንዲታተሙና ለህዝብ ይፋ እንዲሆኑ የሚያስገድድ አንድ ወጥ ህግ የለም፡፡ ሆኖም ስልጣን በሚሰጠው ህግ ላይ የህትመት ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠ እንደሆነ በአስተዳደር መ/ቤቱ ላይ አስገዳኝነት አለው፡፡nበኢትዮጵያ ውስጥ ከአዋጅና ደንብ በስተቀር በአስተዳደር መ/ቤቶች በየጊዜው የሚወጡት ስፍር ቁጥር የሌላቸው መመሪያዎች በነጋሪት ጋዜጣ አይታተሙም፡፡ ስልጣን የሚሰጠው አዋጅም በስተቀር ህትመትን እንደቅድመ ሁኔታ አያስቀምጥም፡፡o

የህብረህዋሳት ልገሳና ንቅለ ተከላ።

የህብረህዋሳት ልገሳና ንቅለ ተከላ፣ 

የህብረህዋሳት ልገሳና ንቅለ ተከላ የመድሀኒት፣ 

የምግብና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ደንብ ቁ. 299/2006 አንቀጽ 58-62 ድንጋጌዎች ስለ ደምና ደም ተዋጽኦ እና የሰውነት አካል ክፍሎችና የህብረህዋሳት ልገሳና ንቅለ ተከላ (donation of blood and blood products and donation and transplantation of organs and tissues) የሚከናወንባቸውን ሁኔታዎች ይደነግጋሉ፡፡ ደንቡ የወጣው የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 661/2002 አንቀጽ 55/1/ እና አሁን በአዋጅ ቁ. 916/2008a በተተካው አዋጅ ቁ. 691/2003b አንቀጽ 5 ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በተሰጠ ስልጣን እንደሆነ በመግቢያው ላይ ተመልክቷል፡፡ አዋጅ ቁ. 661/2002 የአካላት ልገሳና ንቀለ ተከላ የሚመለከት ድንጋጌ አልያዘም፡፡ አንቀጽ 55/1/ ም/ቤቱ የሰጠው ስልጣን አዋጁን ለማስፈጸም የሚረዱ ደንቦች እንዲያወጣ ብቻ ነው፡፡ አዋጁ በዝምታ ያለፈውን ለዛውም ንቀለ ተከላን የሚያክል ትልቅ አገራዊ ጉዳይ በማስፈጸም ሰበብ በደንብ መወሰን የፓርላማን ቦታ መቀማት እንጂ በውክልና ህግ የማውጣት ተግባር (delegated legislation) አይደለም፡፡እንደ ተጨማሪ የስልጣን ምንጭ የተጠቀሰው የአዋጅ ቁ. 691/2003 አንቀጽ 5 ትንሽ አግራሞት መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ይዘቱ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 77 የተመለከተው ይሆናል፡፡ህገ መንግስት ጠቅሶ ህግ ማውጣት የሚችለው የተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ነው፡፡ በአንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 13 እንደሰፈረው የሚኒስትሮች ም/ቤት የተወካዮች ም/ቤት በሚሰጠው ስልጣን መሰረት ደንብ የማውጣት ስልጣን አለው፡፡ ስልጣን በማስተላለፍ የሚፈጠረው የወካይ-ተወካይ ግኝኑነት ሚኒስትሮችን ከአስፈፃሚነት በተጨማሪ የህግ አውጭነት ሚና ያላብሳቸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በውክልና የተላለፈ ስልጣን በሌለበት የሚወጣ ማንኛውም ደንብ የህጋዊነትና ህገ መንግስታዊነት ገደቦችን ይጥሳል፡፡ከላይ በምሳሌነት የተጠቀሱት አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የህጋዊነትና የህገ መንግስታዊነት ችግር ያንጸባርቃሉ፡፡ ውጤታማ የቁጥጥር ስልቶች ባልተረዘጉበት ሁኔታ በየጊዜው የሚወጡት መመሪያዎችና ደንቦች በስም ‘የበታች ህጎች’ በተግባር ግን ‘የበላይ ህጎች’ ሆነዋል፡፡

MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስርዓትስነ- የህብረህዋሳት ልገሳና ንቅለ ተከላ። Definitions of the ConstitutionCRIMINAL PROCEDURE RULES AND DISCIPLINE PROCEDURESCRIMINAL PROCEDURE CODES MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE

MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስርዓትስነ- የህብረህዋሳት ልገሳና ንቅለ ተከላ። Definitions of the ConstitutionCRIMINAL PROCEDURE RULES AND DISCIPLINE PROCEDURESCRIMINAL PROCEDURE CODES

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE HOME.

Definitions of the Constitution

CRIMINAL PROCEDURE RULES AND DISCIPLINE PROCEDURES CRIMINAL PROCEDURE CODES

Definitions of the Constitution
CRIMINAL PROCEDURE RULES AND DISCIPLINE PROCEDURES
CRIMINAL PROCEDURE CODES

በህግ የተቀመጠ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት

ህግ የተቀመጠ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት

auction or justice – gavel on the wooden table

በህግ የተቀመጠ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት

በአገራችን ወጥ የአስተዳደር ህግ ባይኖርም የአስተዳደር መ/ቤቶች በግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ እርምጃ የሚወስዱት ሁለወጊዜ በዘፈቀደ አይደለም፡፡ ይብዛም ይነስም በተለያዩ ዝርዝር ህጎች ላይ የስነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች ተደንግገዋል፡፡ ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ ከክስ መሰማት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ድረስ የአስተዳደር መ/ቤቶች የሚከተሉት ስነ ስርዓት በዚህም ፍትሐዊነት የሚገለጽበት መንገድ ደረጃው ይለያያል፡፡ በአንዳንዶቹ ጠበቅ ያለና መደበኛነት የሚታይበት ሲሆን በሌሎቹ ደግሞ ቀላል እና ‘ልል’ ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ነው፡፡

ከሞላ ጎደል ሁሉንም የመሰማት መብት እና የኢአድሎአዊነት መርሆዎች ያሟላ በዓይነቱ በአሜሪካው የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ ላይ ‘መደበኛ’ ተብሎ የተገለጸውን የአስተዳደር ዳኝነት የሚመስል የክርክር ስርዓት የሚገኘው የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ ቁ. 847/2006 ላይ ነው፡፡ ስርዓቱ የተዘረጋው ህግን በመተላለፍ ጥፋት በሚፈጽም ኦዲተር ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ነው፡፡ ከክስ አመሰራረት እስከ ውሳኔ አሰጣጥ ድረስ የክርክሩ አመራር ስርዓት በአዋጁ ከአንቀጽ 38-43 ባሉት ድንጋጌዎች የሚመራ ሲሆን ሂደቱ አጠር ተደርጎ ሲጠቃለል የሚከተለውን ይመስላል፡፡

አዋጁ የኢ-አድሎአዊነት መርህን ለማረጋገጥ የሚና መደበላለቅን አስቀርቷል፡፡ የመርማሪነት፣ ከሳሽነት እና ውሳኔ ሰጭነት ሚናዎች በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ሰራተኛ/ተሿሚ ተለይተው ተከፋፍለዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ‘መርማሪ ሹም’ የሚባል የቦርዱ ተቀጣሪ ሠራተኛ ወይም ከቦርዱ ጋር የቅጥር ግንኙነት ያልመሰረተ ብቃት ያለው ባለሞያ የምርመራ ተግባር ያከናውናል፡፡ መርማሪ ሹሙ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ሲያምንበት ክስ እንዲመሰረት ለቦርዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የውሳኔ ሀሳብ ከማቅረብ ውጪ በራሱ ክስ አያቀርብም፡፡ በአዋጁ የከሳሽነት ሚና የተሰጠው ለስራ አስፈፃሚው ነው፡፡ ስራ አስፈፃሚው ክስ ለመመስረት ከወሰነ በምርመራ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ያልነበሩ ከመካከላቸው አንዱ የህግ ባለሞያ የሆነ ሶስት የቦርዱን ሰራተኞች በክስ ሰሚነት ይሰይማል፡፡ እነዚህ ክስ ሰሚዎች (hearing examiners) ክርክሩን ሰምተው የመጨረሻ ውሳኔ የማስተላፍ ስልጣን አላቸው፡፡

የዲሲፕሊን ክስ የቀረበበት ሰው ስለቀረበበት ክስ ይዘት የማወቅ እና በራሱ ወይም በጠበቃው አማካኝነት ቀርቦ ማስረጃውን የማቅረብ፣ ምስክሮቹን በመጥራት ቀጥተኛ ጥያቄ መጠየቅና እና ለከሳሽ ምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅ መብቱ በአዋጁ አንቀጽ 39/2/ ተጠብቆለታል፡፡ በግራ ቀኙ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች በተጨማሪ ክስ ሰሚዎች ለጉዳዩ አወሳሰን ጠቃሚ ማስረጃ ይዞ የሚገኝ ማንኛውም ሰው በመጥሪያ በመጥራት በቃለ መሀላ የማረጋገጫ ቃሉን መቀበልና አግባብነት ያላቸውን ሰነዶችና ማስረጃዎች እንዲያቀርብ የማስገደድ ሰፊ ዳኝነታዊ ስልጣን ተጎናጽፈዋል፡፡ ክስ ሰሚዎች በክርክሩ ሂደት የቀረቡትን ማስረጃዎችና ክርክሩን ከመረመሩ በኋላ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ አዋጁንና በአዋጁ መሰረት የወጣን ደንብና መመሪያ መተላለፍ አለመተላፉን ይወስናሉ፡፡ የህግ መተላለፍ ከተፈጸመ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ጀምሮ እስከ ፈቃድ መሰረዝ ብሎም እስከ 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና ሌሎች በአዋጁ ላይ የተዘረዘሩ አስተዳደራዊ ቅጣቶችን ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡

ከሞላ ጎደል ተቀራራቢ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በሚወስዳቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች ላይ ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡ በሲቪል አቪዬሽን አዋጅ ቁ. 616/2001 አንቀጽ 80/1/ ላይ እንደተደነገገው ባለስልጣኑ አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ሊወስደው ስላሰበው እርምጃ ለሚመለከተው ሰው ማሳወቅና እርምጃው ሊወሰድ አይገባም የሚልበትን ምክንያት እንዲያስረዳ ዕድል መስጠት አለበት፡፡ ማስታወቂያው ጥፋት መፈጸሙን የሚገልጽ ክስ ሳይሆን በምርመራ ግኝት ባለስልጣኑ ድምዳሜ ላይ ከደረሰ በኋላ ድምዳሜውን ለማስተባበል የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡ ስለሆነም በምርመራ ሂደት ባለስልጣኑ የሚሰማቸውን ምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅ ዕድል አይኖርም፡፡ ሆኖም ቀጣይ የአዋጁ አንቀጽ 80/4/ ድንጋጌ በጠበቃ ወይም በባለጉዳዩ በራሱ ክርክር የማሰማት መብትን የሚፈቅድ እንደመሆኑ ማስረጃ የማቅረብና ምስክር ማሰማት የስነ ስርዓቱ አካል አድርጎ መቁጠር ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የባለስልጣኑ ሠራተኛ የግል ጥቅሙን በሚነካ ጉዳይ በምርመራ ሂደት እንዳይሳተፍ ገደብ የሚጥለው የአዋጁ አንቀጽ 80/3/ በከፊልም ቢሆን ከአድልኦ የፀዳ ውሳኔ እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

የአስተዳደር መስሪያ ቤት ህግን በማስከበር ስልጣኑ በቀጥታ ከሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎችና ከሚወስዳቸው እርምጃዎች በተጨማሪ በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴ ዳኝነታዊ ተግባራት ሲያከናውን ጠበቅ ያለ ስርዓት ይከተላል፡፡ በኢትዮጵያ የውሀ ሀብት አስተዳደር አዋጅ ቁ. 197/1992 የማዕከል ውሀ ሀብት አስተዳደርን አስመልክቶ የቁጥጥር ተግባራት እንዲያከናውን ስልጣን የተሰጠው ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የውሀ ግልጋሎት ፈቃድ የተሰጣቸው ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ከፈቃዱ ጋር የተያያዙ መብትና ግዴታዎችን አስመልክቶ በመካከላቸው የሚነሱ ክርክሮችን እንዲሁም በባለ ፈቃድ እና በሌላ ሶስተኛ ወገኖች መካከል የሚፈጠሩ ማናቸውንም ክርክሮች ሰምቶ የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በውክልና በሰጠው የህግ አውጭነት ስልጣን መሰረት ክርክሮቹ የሚመሩበት ስርዓት በደንብ ቁ. 115/1997a ተደንግጓል፡፡

በተቆጣጣሪው ባለስልጣን ዘንድ በሚካሄደው የክርክር አመራር ስርዓት ላይ መደበኛው የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ ተፈጻሚነት አለው፡፡ በደንቡ ላይ ተለይተው የተቀመጡት ጥቂት የስነ-ስርዓት ድንጋጌዎችም ቢሆኑ ጠበቅ ያሉ ናቸው፡፡ በዚህ የተነሳ በተቆጣጣሪው አካል የሚካሄደው ክርክር በይዘቱ ፍርድ ቤቶች ከሚከተሉት የሙግት ስርዓት ጋር ይቀራረባል፡፡

ክርክሩ የሚጀመረው አቤት ባዩ በሚያቀርበው ማመልከቻ ነው፡፡ ማመልከቻው የክርክሩን ፍሬ ሀሳብ (በእንግሊዝኛው ቅጂ memorandum summarizing the dispute) እና ማስረጃ እንዲሁም የአቤት ባዩን ቅሬታ እና እንዲሰጥለት የሚፈልገውን ውሳኔ አካቶ መያዝ ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም በይዘቱ ከመደበኛው የክስ አቤቱታ ብዙም አይለይም፡፡ ተቆጣጣሪው አካል ማመልከቻውን እንደተቀበለ ክርክሩ የሚሰማበትን ቦታና ጊዜ የሚገልጽ መጥሪያና የማመልከቻ ቅጂ ለተከሳሹ እንዲደርሰው ያደርጋል፡፡ በቀጠሮ ቀን ባለጉዳዮች በቀጠሮ ሰዓትና ቦታ ተገኝተው ጉዳያቸውን ያስረዳሉ፡፡ ማስረጃም ያቀርባሉ፡፡ በሁለቱም ወገኖች የሚቀርቡ ማስረጃዎች በተቆጣጣሪው አካል ይመዘገባሉ፡፡ ተከሰሹ መጥሪያ ደርሶት ካልቀረበ ጉዳዩ በሌለበት ይሰማል፡፡ ተቆጣጣሪው ጉዳዩን ሰምቶ የሚሰጠውን ውሳኔ ባለጉዳዮች እንዲያውቁት ማድርግ ያለበት ሲሆን በተጨማሪም የውሳኔውን መዝገብ ግልባጭ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

በደንቡ ላይ ለውሳኔ ምክንያት መስጠት እንደ ቅድመ ሁኔታ አልተቀመጠም፡፡ ይሁን እንጂ ተቆጣጣሪው እንደ አግባብነቱ የፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ህጉን ተፈጻሚ የማድረግ ግዴታ ያለበት እንደመሆኑ ምክንያት የጎደለው ውሳኔ በፍርድ ቤት መሻሩ አይቀርለትም፡፡

የመሰማት መብት በህጉ ቢፈቀድም በጥቅል አነጋገር በሚገለጽበት ጊዜ የመብቱን ወሰን አፈጻጸም አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን የክፍያ መ

ፈጸሚያ ተቋምን ወይም የግብይት ፈጻሚዎችን ወይም የማህበራቸውን ዕውቅና ከማገዱ ወይም ከመሰረዙ በፊት መጀመሪያ የተቋሙ ኃላፊዎች በማስታወቂያ እንዲያውቁት ማድረግና ለባለጉዳዩ የመሰማት ዕድል መስጠት ይኖርበታል፡b የድንጋጌው አነጋገር የጠቅላላነት ባህርይ ቢታይበትም የመሰማት መብት መሰረታዊ የአስተዳደር ፍትሕ ጥያቄ እንደመሆኑ ዕውቅና ከመታገዱ ወይም ከመሰረዙ በፊት ቅድመ ክስ ማስታወቂያ፣ ማስረጃ የማቅረብ መብትና ተቃራኒ ማስረጃ የማስተባበል መብት ተሟልተው ሊገኙ ይገባል፡፡

ከላይ ያየነው ዓይነት ከመደበኛ ፍርድ ቤት ጋር የሚቀራረብ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት አፈጻጸሙ በውስን አስተዳደራዊ ክርክሮች ላይ ብቻ ነው፡፡ በጣም በርካታ መ/ቤቶች ለስነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች የሚገዙት በጣም በስሱ ነው፡፡ አብዛኛው ቀዳሚ ውሳኔ /initial decision/ በአስተዳደራዊ የሙግት ሂደት ስር አያልፍም፡፡ ውሳኔ አሰጣጡ በባህርዩ መርማሪ ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከተውን አካል አያሳትፍም፡፡ ህግ መጣሱ የሚረጋገጠው መ/ቤቱ በሚቀርብለት ጥቆማ ወይም በራሱ አነሳሽነት በሚያካሂደው ምርመራና ማጣራት አማካይነት ነው፡፡ በዚህ መልኩ ጥፋት መፈጸሙ አስቀድሞ አቋም ይያዝበታል፡፡ ሆኖም መ/ቤቱ የደረሰበት ድምዳሜ አስገዳጅነት ወዳለው የመጨረሻ ውሳኔ ከመሸጋገሩ በፊት የሚመለከተው አካል አስተያየት ወይም ምላሽ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡ መልስ ሰጭው የቀረበበትን ማስረጃ የማስተባበል አሊያም ተቃራኒ ማስረጃ የማቅረብ በህግ የተጠበቀ መብት የለውም፡፡

ልል የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት ከሚደነግጉ ህጎች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በመድን ሰጪ ድርጅት ያካሄደው ምርመራ የመጨረሻ ሪፖርት ከመዘጋጀቱ በፊት ለተመርማሪው መድን ሰጪ ድርጅት እንዲደርሰው ተደርጎ በሪፖርቱ ላይ አስተያየቱን እንዲያቀርብ ዕድል ይሰጠዋል፡፡c

/ንግድና ኢንዱስትሪ/ ሚኒስቴሩ ወይም የእርሱ ተወካይ የአንድ ባለዕቃ ማከማቻ ቤት የግብርና ምርት ውጤቶች ተቆጣጣሪ፣ መዳቢ፣ ደረጃ ሰጪ፣ መዛኝ ወይም ናሙና አውጭ የሥራ ፈቃድ ለዘለቄታው እንዲሰረዝ ከመወሰኑ በፊት አጥፍቷል የተባለው ጥፋት በጽሑፍ እንዲገለጽለትና በቂ ጊዜ ተሰጥቶት በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት ወይም መቃወሚያ እንዲያቀርብበት ዕድል ሊሰጠው ይገባል፡፡d

በአንዳንድ ህጎች ላይ ደግሞ የመሰማት መብት ውሳኔውን በማሳወቅ ላይ ብቻ ይገደባል፡፡ በእርግጥ ውሳኔው አግባብ እንዳልሆነ በቃል ሆነ በጽሑፍ ማስተባበል ካልተቻለ የመሰማት መብት መነፈጉን እንጂ በከፊል መገደቡን አይደለም የሚያሳየው፡፡ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴሩ የዕፅዋት አዳቃዮችን መብት ለመሰረዝ ውሳኔ ላይ ከደረሰ ለመሰረዝ የበቃበትን ምክንያት በመግለጽ ለባለመብቱ የጽሑፍ ማስታወቂያ መስጠትና መብቱ የተሰረዘ መሆኑን ለሕዝብ ማስታወቅ አለበት፡፡e ማስታወቂያው የመሰረዝ ውሳኔውን ከማሳወቅ የዘለለ ውጤት የለውም፡፡ ባለመብቱ የእርምጃውን ህጋዊነት ለመቃወም የሚችልበት ቀዳዳ የለም፡፡

አንዳንድ ጊዜ የመሰማት መብት የሚፈቀደው ከውሳኔ በኋላ ይሆናል፡፡ የዘር አስመጪ፣ ላኪ፣ የዘር አምራች፣ አዘጋጅ፣ ጅምላ ሻጭ፣ አከፋፋይ ወይም ቸርቻሪ በዘር አዋጅ ቁ. 782/2005 አንቀጽ 21/1/ እና /2/ መሰረት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ወይም በክልል ባለስልጣን ከመታገዱ ወይም ከመሰረዙ በፊት በድንጋጌው ላይ የተጠቀሱት በቂ ምክንያቶች እውነት ስላለመሆናቸው ለማስረዳትና ተቃራኒ ማስረጃ ለማቅረብ ዕድል አልተሰጠውም፡፡ ሆኖም ከውሳኔው በኋላ ውሳኔውን ለሰጠው አካል አስተዳደራዊ ቅሬታ የማቅረብ መብቱ በአንቀጽ 25/1/ ተጠብቆለታል፡፡ አመልካቹ በተሰጠው ምላሽ ካልረካ ቅሬታውን ለሚመለከታው የፍትሕ አካል ሊያቀርብ እንደሚችል በድንጋጌው ንዑስ አንቀጽ 2 ተመልክቷል፡፡

ህገ መንግስታዊ የመሰማት መብት?

ህገ መንግስታዊ የመሰማት መብት?

የተፈጥሮ ፍትሕ በእንግሊዝና ሌሎች ኮመን ሎው አገራት በዳኞች የዳበረ የፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርህ ነው፡፡ ይህ መርህ በህግ በግልጽ እንደ ቅድመ ሁኔታ ባይቀመጥም ዳኞች ተፈጻሚ እንዳያደርጉት አያግዳቸውም፡፡ በአሜሪካ እንዲሁ ህገ መንግስታዊ ዕውቅና ያገኘው ዱ ፕሮሰስ ኦፍ ሎው (Due Process of Law) በመባል የሚታወቀው ህገ መንግስታዊ መርህ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን የሚገዛ ልዩ ህግ ባይኖርም እንኳን ፍርድ ቤቶች እንደ አግባብነቱ ተፈጻሚ ያደርጉታል፡፡ ሆኖም በእነዚህ ሁለት አገራት ሆነ በሌሎችም ዘንድ አስተዳደር የሚመራበት ስነ ስርዓት ምንጩ በህግ አውጪው የሚወጣ ህግ ነው፡፡

ግልጽ የህግ ድንጋጌ ካለ የስነ-ስርዓት ጉድለት ያለበት ውሳኔ በፍርድ ቤት ሊሻር ወይም ሊሰረዝ እንደሚገባው አያጠራጥርም፡፡ አስገዳጅ የህግ ድንጋጌ ከሌለስ? ፍርድ ቤቶቻችን እንደ እንግሊዝና አሜሪካ ፍርድ ቤቶች ፍትሐዊ የውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎችን ማዳበርና ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው? ካለባቸውስ አቋማቸው ህገ መንግስታዊ መሰረት አለው? በአስተዳደራዊ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት የመሰማት መብት እንዲሁም ኢ-አድሎአላዊነት መርህ በህግ በግልጽ ባልተደነገገበት ሁኔታ የስነ-ስርዓት ጉድለት ያለበት አስተዳደራዊ ውሳኔ ዕጣ ፋንታ መወሰን በብዙ መልኩ ከባድ ነው፡፡

በአንድ በኩል ፍርድ ቤቶች የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት መብት የማረጋገጥ ህገ መንግስታዊ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ህጉን ከማንበብና ከመተርጎም ባለፈ ህግ መጻፍ ህገ መንግስታዊ ሚናቸው አይፈቅድላቸውም፡፡ በዚህ መልኩ የሚፈጠረው ‘ህገ መንግስታዊ አጣብቂኝ’ ብርታትና ጥንቃቄ ካልታከለበት በቀላሉ አይፈታም፡፡ በተጨማሪም ‘መርህ’ በተጨባጭ ‘መሬት ሲወርድ’ ከልዩ ሁኔዎች ጋር ሊጣጣምና የተፈጻሚነት ወሰኑ በአግባቡ ሊሰመር ይገባል፡፡ የመሰማት መብት የግድ የሚልበት ሁኔታ ቢኖርም ከተግባራዊ ፋይዳውና ውጤታማ አስተዳደር አንጻር የሚገደብባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ በተጨማሪም የተፈፃሚነቱ ወሰን የግለሰብ መብት ወይም ጥቅም በሚነካ የዳኝነታዊ ባህርይ ባለው አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ ብቻ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየን አስቸጋሪው ስራ የፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎችን በጠቅላላው መቀበሉ ሳይሆን እንደ ጉዳዩ አይነት ልዩ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የተፈጻሚነቱን አድማስ መለየቱ ላይ ነው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 43511a በ2005 ዓ.ም. በሰጠው ፈር ቀዳጅ የህግ ትርጉም መሰረት አስገዳጅ የህግ ድንጋጌ ባይኖርም ከፊል የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል የመሰማት መብትን የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ የችሎቱን አቋም በጥልቀት ለመረዳት በሐተታው ክፍል የሰፈረውን የሚከተለውን አስተያየት ማየቱ ተገቢ ነው፡፡

…የመሰማት መብት በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ሊከበር የሚገባው መብት ነው፡፡ የመሰማት መብት ከመጀመሪያው ክርክር ጀምሮ እስከመጨረሻው የዳኝነት ሰጪ አካል መከበር ያለበት ስለመሆኑ በሕገ መንግስቱና ስለ ክርክር አመራር በተደነገጉት እንደፍትሐብሔር ስነ ስርአት አይነት ሕጎች ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡

የችሎቱ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ዜጎች ሀሳባቸው ሳይደመጥ መብትና ጥቅማቸውን የሚጎዳ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዳይሰጥባቸው ከለላ በማጎናጸፍ ረገድ ህገ መንግስታዊ ፋይዳው ‘ታሪካዊ’ ሊሰኝ የሚችል ነው፡፡ ከዚያም አልፎ ለአገራችን የአስተዳደር ህግ ዕድገት ችሎቱ ካደረጋቸው አስተዋጽኦዎች መካከል ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል፡፡ በእርግጥ የውሳኔው ፋይዳ ብቻውን በቁሙ መለካት በተግባር ያስከተላቸውን ለውጦች በማጋነን ያስተቻል፡፡ የሰ/መ/ቁ. 43511 አስተዳደሩ አካሄዱን ከችሎቱ አቋም ጋር እንዲያስተካክል በዚህም የመሰማት መብትን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ አካል አድርጎ እንዲያቅፍ የፈጠረው ጫና ሆነ በተግባር ያስከተለው ተጨባጭ ለውጥ የለም፡፡ አስገዳጁን የህግ ትርጉም መቀበልና መተግበር ያለባቸው የስር ፍርድ ቤቶችም ቢሆኑ በአስተዳደራዊ ክርክሮች የመሰማት መብትን በትጋት እንዲያስከብሩ የለውጥ ምንጭ አልሆነላቸውም፡፡ ምናልባትም ውሳኔው ስለመኖሩ ራሱ ገና አልሰሙ ይሆናል፡፡ የሰበር ውሳኔዎች የተደራሽነት ችግር እንዲሁም በውሳኔዎቹ ላይ ጠንካራ ምሁራዊ የሀሳብ ልውውጥ ባህል አለመዳበር በርካታ አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች በቅጾች መጽሐፍ ውስጥ ተቀብረው እንዲረሱ ያደርጋቸዋል፡፡

የሰ/መ/ቁ. 43511 ከህገ መንግስታዊ ፋይዳው ባሻገር ክርክሩ የተጓዘበት መስመር ትኩረት ይስባል፡፡ የክርክሩ መነሻ አመልካቾች ከአዋጅ ውጪ የተወረሰ ቤት እንዲመለስላቸው ለኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ያቀረቡት አቤቱታ ሲሆን ኤጀንሲውም ተጠሪ ምላሽ እንዲሰጡበት ካደረገ በኋላ ማስረጃና ክርክሩን ሰምቶ ቤቱ እንዲመለስላቸው ወስኗል፡፡ በውሳኔው ባለመስማማት ተጠሪ ለኤጀንሲው ቦርድ ይግባኝ በማቅረባቸው ቦርዱ የኤጀንሲውን ውሳኔ ሽሮታል፡፡ ከመሻሩ በፊት ግን አመልካቾችን ጠርቶ ክርክራቸውን አልሰማም፡፡

በመቀጠል አመልካቾች የመሰማት መብታቸው አለመጠበቁን በመግለጽ በቀጥታ የሰበር አቤቱታ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰ/ችሎት ያቀረቡ ቢሆንም አጣሪ ችሎቱ የቦርዱን ውሳኔ የማረም ስልጣን እንዳልተሰጠው በመግለጽ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ አመልካቾች ተስፋ ባለመቁረጥ ጉዳዩ ህገ መንግስታዊ ትርጉም እንደሚያስነሳ በመጠቆም ለህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ አመለከቱ፡፡ እዛም ተቀባይነት አጡ፡፡ አሁንም ሰሚ ፍለጋ ‘አቤት!’ ማለታቸውን ባለማቆም ጉዳያቸውን እንዲያይላቸው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ አቀረቡ፡፡ በመጨረሻ ጥያቄያቸው ፍሬ አግኝቶ የአጣሪ ችሎቱ ውሳኔ ተሻረ፡፡

አመልካቾች ተስፋ ባለመቁረጥ እስከ ፌዴሬሽን ም/ቤት ድረስ ዘልቀው ድል መጎናጸፋቸው በራሱ የተለየ ስሜት ቢያጭርም በተለየ መልኩ ትኩረት የሚስበው ግን የክርክሩ ሂደት ሳይሆን የም/ቤቱ ውሳኔ ይዘት ነው፡፡ የሰበር ችሎት የዳኝነት ስልጣንን በማስፋት አዲስ ህገ መንግስታዊ መልክ ያላበሰው ይኸው ውሳኔ የሰበር ችሎት የቦርዱን መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን እንዳለው አረጋግጧል፡፡ የም/ቤቱ ህገ መንግስታዊ ትርጓሜ መነሻ ያደረገው የኤጀንሲው ቦርድ ዳኝነታዊ ስልጣን ነው፡፡ ስለሆነም ቦርዱ የዳኝነት መሰል አካል (quasi judicial body) በመሆኑና ይህ አካል የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር ስልጣኑ ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለው፡፡

የስልጣን ጥያቄው እልባት ካገኘ በኋላ መዝገቡ ከፌዴሬሽን ም/ቤት ወደ ሰበር ችሎት ሲመለስ የቦርዱ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት መሰረታዊ ጭብጥ ሆኖ ተነስቷል፡፡ ጭብጡን ለመፍታት ችሎቱ የቦርዱን የማቋቋያ አዋጅb የተመለከተ ቢሆንም በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ቦርዱ የተከራካሪዎችን የመሰማት መብት እንዲጠብቅ የሚያስገድድ ድንጋጌ አላገኘም፡፡

በአስተዳደራዊ ክርክሮች ላይ የመሰማት መብት የሚጠብቅ ህግ በሌለበት ሁኔታ ውሳኔው ሰጭው አካል በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት መብቱን እንዲያከብር ግዴታ መጫን ለችሎቱ ፈታኝ ስራ እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ ምክንያቱም ከህግ የመነጨ ግዴታ በሌለበት ቦርዱ የመሰማት መብት መርሆዎችን እንዲከተል ማስገደድ በውጤቱ የችሎቱን ተግባር ከህግ መተርጎም ወደ ‘ህግ መጻፍ’ ያሸጋግረዋል፡፡ ስለሆነም ችሎቱ በስልጣን ክፍፍል መርህ የተሰመረውን ድንበር ሳይሻገር በራሱ የዳኝነት ስልጣን ዛቢያ ውስጥ ሆኖ ውሳኔውን በአሳማኝ ምክንያት ማስደገፍ አለበት

የኢ-አድሎአዊነት መርህ

የኢ-አድሎአዊነት መርህ
ከአድልኦ የፀዳ ፍርድ (The rule against bias) የሚለው መርህ በኮመን ሎው አገራት በስፋት የዳበረ መሰረተ ሀሳብ ሲሆን በአጭሩ ሲገለጽ አንድ ሰው በራሱ ጉዳይ ራሱ ከሳሽ ራሱ ዳኛ መሆን የለበትም እንደማለት ነው፡፡ ኢ-አድሎአዊነት አብዛኛውን ጊዜ ራሱን የቻለ የተፈጥሮ ፍትህ መርህ ተደርጐ ቢጠቀስም በተግባር ሲታይ ግን በመሰማት መብት ውስጥ የሚጠቃለል የፍትሐዊ ስነ-ስርዓት አንድ አካል ነው፡፡ አንድ ሰው በአስተዳደር ጉባዔ (Administrative Tribunal) ፊት ቀርቦ የመሰማት እድል ሊሰጠው ይገባል ሲባል በውስጠ ታዋቂነት ፍ/ቤቱ ከአድልኦ የፀዳ እንደሆነ ግምት በመውሰድ ነው፡፡
ፍርደ ገምድል ያልሆነ፤ ያልተዛባ ውሳኔ መኖር ህዝቡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያለውን አመኔታ የሚያንፀባርቅ እንደመሆኑ ተፈፃሚነቱም /በተለይ በኮመን ሎው አገራት/ እጅግ ጥብቅ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የታወቁት የእንግሊዝ ዳኛ ሎርድ ሄዋርት እንዲህ ብለው ነበር፡፡
ፍትህ መሰራቱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ፍትህ ሲሰራ ጭምር በማያጠራጥርና ግልጽ በሆነ አኳኋን መታየት መቻል አለበት፡፡
የዳኛው ልጅ ‘ቀማኛ’ ተብሎ በአባቱ ፊት ችሎት ሲቀርብ በእርግጥም በህጉ መሰረት ጥፋተኛ ላይሆን ይችላል፡፡ ጥፋተኛ ካልሆነ መለቀቁ ፍትህ ነው፡፡ ግን ለማንም አይመስልም፡፡ ፍትህ ሲሰራ አይታይምና፡፡ ዋናው ቁም ነገር ዝምድና፤ የገንዘብ ጥቅም ወይም ሌላ ምክንያት በዳኛው ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተጽእኖ አለማድረጉ አይደለም፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች እስካሉ ድረስ ዳኛው ምንም ያህል ንፁህና ጻድቅ ሰው ቢሆን እንኳን በችሎት ላይ ተቀምጦ ሲያስችል አመኔታ ያጣል፡፡ የኢ-አድሎአዊነት መርህ ዋና አላማ ውሳኔ ሰጭው አካል የተዛባ ፍርድ እንዳይሰጥ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም ራሱም ሳያውቀው እንኳን በንፁህ ህሊናው ላይ ተፅእኖ ሊያደርሱ ከሚችሉ ሁኔታዎች ነጻ ሆኖ ዳኝነት እንዲሰጥ ለማስቻል ነው፡፡
ይህ የኢ-አድሎአዊነት መርህ በተለይ በመደበኛ ፍ/ቤት፣ በአስተዳደር ጉባኤ እና ዳኝነታዊ ውሳኔ በሚሰጡ የአስተዳደር መ/ቤቶች ጥብቅ ተፈጻሚነት አለው፡፡ ውሳኔ ሰጪው አካል በያዘው ጉዳይ በህሊናው ላይ ተፅእኖ ሊያመጣ የሚችል ሁኔታ መኖሩን በተረዳ ጊዜ ራሱን ከውሳኔ ሰጪነት ማግለል አለበት፡፡ ይህ ባልሆነበት ጊዜ በቂ ጥርጣሬ ያደረበት ወገን አቤቱታ አቅርቦ ዳኛው እንዲቀየርለት ማመልከት ይችላል፡፡ ሁኔታው መኖሩ የታወቀው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ከሆነ የዛ ውሳኔ እጣ ፈንታ ዋጋ አልባ መሆን ነው፡፡
አድሎአዊ ውሳኔ ተሰጥቷል የሚባለው የውሳኔ ሰጭው ህሊና የተዛባ እንደሆነ ነው፡ ለመሆኑ የሕሊና መዛባት ምን ማለት ነው?
በጥሬ ትርጉሙ ሲታይ ማንኛውም ነገር በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ውሳኔ ሰጭው በነጻ ህሊናው ተመርቶ ሊሰጥ ይችል ከነበረው ውሳኔ በተቃራኒ የተለየ ውሳኔ ላይ ያደረሰ ከሆነ ህሊናው ተዛብቷል ብለን መናገር እንችላለን፡፡ ህሊና ከተዛባ የክርክሩ ውጤት (ማለትም ውሳኔው) ጉዳዩ ከመመርመሩ በፊት ድምዳሜ ተደርሶበታል፡፡ ዳኛው ከከሳሽ ወይም ተከሳሽ ጉቦ ከተቀበለ ፍርዱ ለማን እንደሚሰጥ አስቀድሞ ታውቋል፡፡ በዚህ መልኩ የሚሰጥ ፍርድ በተዛባ ህሊና የተሰጠ አድሎአዊ ፍርድ ነው፡፡
የተዛባ ህሊና ከምንጩ አንፃር በተለያየ መንገድ ይገለጻል፡፡ በዋነኛነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

ልዩ ሁኔታዎችና የተፈጻሚነት ወሰን

ልዩ ሁኔታዎችና የተፈጻሚነት ወሰን
በፍርድ ቤቶች የዳበሩ መሰረታዊ መርሆዎች እንዲሁም አስገዳጅነት ያላቸው የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት ህጎች በሁሉም አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ ወጥ ተፈጻሚነት የላቸውም፡፡ የእያንዳንዱ አስተዳደራዊ ውሳኔ ከግለሰቦች መብትና አንጻር ሲመዘን ከቀላል እስከ ከባድ የሚያስከትለው ውጤት እና ተፅዕኖ ይለያያል፡፡ የውሳኔውም ዓይነት እንዲሁ ወጥ መልክ የለውም፡፡ የመንግስት ሠራተኛን ከስራ ማባረር፣ አስተዳደራዊ ቅጣት መጣል፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከይዞታ ማፈናቀል፣ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (ካርታ) መሰረዝ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ የሙያ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ፣ የስራ ፈቃድ መሰረዝና ማገድ፣ የሊዝ ውል ማቋረጥ፣ በአንድ የስራ ዘርፍ የተሰጠ ዕውቅና (ለምሳሌ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) መሰረዝ እና ሌሎች መሰል ውሳኔዎች ህገ መንግስታዊ ጥበቃ ያገኙ መብቶችን የመጣስ ከፍተኛ አዝማሚያ ስላላቸው ፍትሐዊ ስርዓት ተከትለው መወሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ አስተዳራዊ ቅሬታ እና ይግባኝ የሚስተናገድበት መንገድ እንዲሁ ፍትሐዊ ስነ ስርዓት እና አንጻራዊ ገለልተኘነት ካላንፀባረቀ የይስሙላ ሆኖ ነው የሚቀረው፡፡
ስለሆነም በእነዚህ በተጠቀሱት ምሳሌዎች ስር የሚወድቁና ሌሎች ተመሳሳይ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ለመሰማት መብት እና ኢ-አድሎአዊነት መርሆዎች ተገዢ ሊሆኑ ይገባል፡፡ እንደዛም ሆኖ ግትር ተፈጻሚነት ሊኖራቸው አይገባም፡፡ አስተዳደራዊ አመቺነትን ያላማከለ የሰነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታ ውጤታማነትን ያኮላሻል፡፡ ለምሳሌ በከፊል አስተዳደራዊ ክርክሮች በጠበቃ የመወከል መብት በአስተዳደሩ ላይ ከሚያመጣው ጫና አንጻር እንዲቀር ቢደረግ የመሰማት መብትን አያጣብብም፡፡
ከላይ በምሳሌነት የተጠቀሱት አስተዳደራዊ ውሳኔዎች አንድ የአስተዳደር መ/ቤት በየዕለቱ ይቅርና በየወሩ የሚያከናውናቸው ተግባራት አይደሉም፡፡ በቁጥር በእጅጉ በልጠው የሚገኙት ውሳኔዎች ግዙፋዊ የመብት መጓደል አያስከትሉም፡፡ ሆኖም በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የግለሰቦችን መብትና ጥቅም የሚነኩ ከሆነ በዘፈቀደ መወሰድ የለባቸውም፡፡ ይብዛም ይነስም በተነካው መብት ልክ ፍትሐዊነት በገሀድ እንዲታይ ይጠበቃል፡፡
እስካሁን የቀረበው ዳሰሳ አንድ መሰረታዊ ጥልቅ መልዕክት ያስጨብጠናል፡፡ ይኸውም፤ ማንኛውንም አስተዳደራዊ ውሳኔ ለአንድ ወጥ ስነ ስርዓት ተገዢ ማድረግ ሊሞከር ቀርቶ አይታሰብም፡፡ ፍርድ ቤት ብቻ ነው አንድ ወጥ ስነ-ስርዓት የሚከተለው፡፡ ያላደገ ሆነ የዳበረ የአስተዳደር ህግ ያላቸው አገራት በማንኛውም አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን አንድ ወጥ ስነ ስርዓት የላቸውም፡፡ አንድ አስተዳደራዊ ውሳኔ ከቀላል እስከ ጥብቅ የትኛውን ስነ ስርዓት መከተል እንዳለበት ለመወሰን ለህግ አውጪው አስቸጋሪ ስራ ነው፡፡ ውስብስብ የሆነው የአስተዳደር ስራ ባህርይ በዚህ ረገድ የሚደረገውን ጥረት ፈታኝ ያደርገዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ፈተናው በወጉ ካልተመለሰ ፍትሐዊነትና ውጤታማ አስተዳደር ሚዛናቸውን ይስታሉ፡፡
እንደ ፒተር ዎል አገላለጽ በአስተደደራዊ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ተፈጻሚ የሚሆኑት አነስተኛ የስነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች እንደ ጉዳዩ ዓይነትና ውስብስብነት፣ የማስረጃዎችና የሚረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ዓይነት፣ የውሳኔ ሰጭው ማንነትና የሚያከናውነው የአስተዳደር ተግባር ባህርይ እንዲሁም ውሳኔው በግለሰቦች ላይ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት አንጻር ደረጃቸው ይለያያል፡፡
[W]hat constitutes a minimum compliance with due process in the way of administrative hearing…will vary to a considerable extent with the nature of the substantive right, the character and complexity of the issues, the kinds of evidence and factual material, the particular body or official, and the administrative functions involved in the hearing.a
የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ ፍትሐዊነት እንዲሰፍን ከዚያም አልፎ በህዝብ አስተዳደር ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት በአጠቃላይ መልካም አስተዳደር እንዲያብብና እንዲጎለብት የሚያበረክተው አዎንታዊ አስተዋጽኦ በሀሳብ ሆነ በተግባር ደረጃ ተፈትኖ የተረጋገጠ ቢሆንም አፈጻጸሙ በጥንቃቄ ወሰን ካልተበጀለት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የአስተዳደር ስነ ስርዓት ፍርድ ቤቶች እንደሚከተሉት የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ጥብቅ እና መደበኛ በሆነ ቁጥር አስተዳደራዊው ሂደት እጅና እግሩ ይታሰራል፡፡ በዚህ የተነሳ ዜጎች ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ያጣሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ደግሞ የዜጎችን ብሶት ‘ከፍትሕ ጥማት’ ወደ ‘አገልግሎት ረሀብ’ ቢቀይረው እንጂ ፍሬ አያስገኝም፡፡
እ.ኤ.አ በ1946 በወጣው የአሜሪካው የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ህግ (Administrative Procedure Act) የአስተዳደር ዳኝነት መደበኛ እና ኢ-መደበኛ በሚል ለሁለት ተከፍሏል፡፡ መደበኛው የአስተዳደር ዳኝነት ከክስ መስማት እስከ ውሳኔው ይዘት ድረስ በዝርዝር አስገዳጅ ደንቦች የሚገዛ ሲሆን ኢ-መደበኛው ግን በቀላልና ልል ስርዓት ይመራል፡፡ አስተዳደራዊ አመቺነትን ያማከለው ይህ አካሄድ በአንድ በኩል በዘፈቀደ በሚወሰድ እርምጃ ፍትሕ እንዳይጓደል በሌላ በኩል ደግሞ በጥብቅ ስነ ስርዓት ሳቢያ ውጤታማ አስተዳደር እንዳይሰናከል ህጉ የተከተለው አስታራቂ መስመር ነው፡፡
በመደበኛው የአስተዳደር ዳኝነት ከክስ መሰማት (hearing) ጀምሮ አጠቃላይ ክርክሩ በመዝገብ (on the record) እንዲካሄድ የሚያስገድድ ሲሆን በይዘቱም ጠበቅ ያለ ስርዓት ነው፡፡ ይህ ስርዓት ተፈጻሚ የሚሆነው በልዩ ህግ በግልጽ ተደንግጎ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ህጉ የመደበኛውን የአስተዳደር ዳኝነት የስነ ስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች በመደንገግ ተፈጻሚነቱን ግን ህግ አውጪው በዝርዝር ህግ በግልጽ በወሰናቸው ሁኔታዎች ላይ ብቻ ገድቦታል፡፡b በዚህ መልኩ በመደበኛው የዳኝነት ሂደት የሚያልፉ የአስተዳደር ክርክሮች በቁጥር ከአምስት ፐርሰንት አይበልጥም፡፡c የተቀሩት ኢ-መደበኛውን ስርዓት የሚከተሉ ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር መደበኛው አስተዳደራዊ ክርክር ተፈጻሚነቱ በልዩ ሁኔታዎች ብቻ ነው፡፡
አሜሪካኖች ከሞላ ጎደል ሁሉም አስተዳደራዊ ክርክሮች ኢመደበኛ አካሄድ እንዲከተሉ የመረጡበት ምክንያት ንድፈ ሀሳባዊ ሳይሆን ተጨባጭና ተግባራዊ ነው፡፡ የአስተዳደር መ/ቤቶች እንደ መደበኛ ፍርድ ቤት ክስ እየሰሙ በማከራከር ውሳኔ የሚሰጡ ከሆነ የተቋቋሙለትን ዓላማ መቼም ቢሆን አያሳኩም፡፡ መደበኛ የአስተዳደር ክርክር ከሚፈጀው ጊዜ እንዲሁም ከሚያስፈልገው የሰው ሀይልና የገንዘብ ወጪ አንጻር በሁሉም አስተዳደራዊ ክርክሮች ላይ ተፈጻሚ ቢደረግ ውጤታማ አስተዳደር ይቅርና ‘አስተዳደር’ የሚባል ነገር ራሱ አይኖርም፡፡
በኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም. እና 2001 ዓ.ም. የተዘጋጁት ረቂቅ የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጆች ይህን መሰረታዊ ተጨባጭ እውነታ በቅጡ አልተረዱትም፡፡ ሁለቱም ረቂቆች አስተዳደራዊ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት መደበኛው የክስ መሰማት ስርዓት እንዲከናወን በአስተዳደር መ/ቤቶች ላይ ግዴታ ያስቀምጣሉ፡፡ ከሁለቱ ረቂቆች አንዳቸው ጸድቀው አስገዳጅ ህግ ከሆኑ የአስተዳደር መ/ቤቶች ወደ መደበኛ ፍ/ቤቶች መቀየራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በአሜሪካ በዚህ ዓይነት የክርክር ሂደት የሚያልፉ ጉዳዮ
ች ከአምስት ፐርሰንት አይበልጡም፡፡ የተቀረው 95 ፐርሰንት ኢመደበኛ ነው፡፡ በረቂቅ ህጎቹ የተመረጠው አቅጣጫ ደግሞ ሁሉም (ማለትም 100 ፐርሰንት) አስተዳደራዊ ክርክሮች መደበኛ ስርዓት እንዲከተሉ ያስገድዳል፡፡ በዚህ ሁኔታ አስገዳጅ ህግ ሆነው በተወካዮች ም/ቤት ቢታወጁ ሊከተል የሚችለውን አስተዳደራዊ መንዛዛት ለመገመት ከወደሁ ያስቸግራል፡፡

የመሰማት መብት

የመሰማት መብት
በተከሰሰበት ጉዳይ መልስ ሳይሰጥ እንዲሁም ማስረጃውን ሳያሰማ የንግድ ፍቃዱ የተሰረዘበት ነጋዴ፣ የቤት ካርታው የመነከበት ግለሰብ፣ ከዩኒቨርሲቲ የተባረረ ተማሪ… ሁሉም የአስተዳደር በደል ሰለባዎች ናቸው፡፡ የአንድን ግለሰብ መብትና ጥቅም ሊጐዳ የሚችል ማንኛውም አስተዳደራዊ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ግለሰቡ የመሰማት ዕድል ሊያገኝ ይገባል፡፡ የመሰማት መብት በዘፈቀደ በሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ የተነሳ ዜጎች ህይወታቸውና ንብረታቸው ለአደጋ እንዳይጋለጥ ይከላከላል፡፡
መሰማት ሲባል ከክስ እስከ ውሳኔ ድረስ ያሉ ዝርዝር የክርክር ሂደቶችን ያቅፋል፡፡ እያንዳንዱ ሂደት በራሱ ካልተሟላ በቂ የመሰማት ዕድል እንዳልተሰጠ ይቆጠራል፡፡ በአስተዳደር ዳኝነት ውስጥ የዚህ መብት ዝርዝር ሂደቶችና አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች በዋነኛነት የሚከተሉትን ያካትታል፡፡
ቅድመ-ክስ ማስታወቂያ
የክስ መሰማት ውሳኔ ሰጭው ባለስልጣን ለባለጉዳዩ /ለተከሳሹ/ በሚሰጠው የክስ ማስታወቂያ ይጀመራል፡፡ ማስታወቂያ ተከራካሪው እንዲቀርብ የሚሰጥ መጥሪያ ነው፡፡ በይዘቱ ባለጉዳዩ የቀረበበትን ክስ በሚገባ ተረድቶ መልሱን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ የሚያስችለው በቂ ማስታወቂያ መሆን አለበት፡፡ ተከራካሪው ራሱን ለመከላከል የሚችለው የተከሰሰበትን ጉዳይ በማያሻማ ሁኔታ የተገለጸለት እንደሆነ ነው፡፡a ከዚህ አንጻር የክሱ ዓይነትና ምክንያት ቀጥተኛና ግልጽ በሆነ መንገድ በማስታወቂያው ላይ መስፈር ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ እንዲቀርብ የተጠራው ባለጉዳይ የመንግስት ሰራተኛ ወይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆነ በደፈናው ‘የዲሲፕሊን ክስ ስለቀረበብህ እንድትቀርብ!’ የሚል መጥሪያ ግልጽነት ይጐድለዋል፡፡ በተጨማሪም ከአንድ በላይ ክስ በቀረበ ጊዜ እያንዳንዱ ክስ በዝርዝር ሊገለጽ ይገባል፡፡ በሌላ መልኩ በክስ ማስታወቂያው ላይ የቀረበው የክስ አይነት ክሱ በሚሰማበት ቀን የተቀየረ እንደሆነ ክሱ እንዳልተገለጸ ወይም በቂ ማስታወቂያ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል፡፡ በስርቆት ተከሶ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ፊት እንዲቀርብ የተጠራ ተማሪ ክሱ በሚሰማበት ቀን የመጀመሪያው ክስ ተቀይሮ ‘በፈተና ማጭበርበር’ ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ ተማሪው የተቀጣው በቂ ማስታወቂያ ሳይሰጠው እንደመሆኑ ቅጣቱ መሰረታዊ የሆነውን የመሰማት መብት ይጻረራል፡፡
ክሱ የሚሰማበት ጊዜና ቦታ
‘በቂ’ ሊባል የሚችል የክስ ማስታወቂያ መለኪያ ባለጉዳዩ ራሱን በሚገባ እንዲከላከል በሚያስችል መልኩ በቂ መረጃና ጊዜ የሰጠ እንደሆነ ነው፡፡ ክርክሩን ለማካሄድ ስልጣን የተሰጠው አካል ተከራካሪዎች የሚመቻቸውን ጊዜ በመወሰን ክሱ ስለሚሰማበት ቦታ ትክክለኛ መረጃ እንዲኖራቸው በሚያስችል መልኩ መጥሪያውን መላክ ይጠበቅበታል፡፡ ጊዜው ሲገለጽ ትክክለኛው ሰዓት ጭምር መገለጽ አለበት፡፡ ቦታውም እንዲሁ ትክክለኛ መለያ አድራሻውን በመጥቀስ ለባለጉዳዩ/ለተከሳሹ በግልጽ ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡
ከጊዜ ጋር በተያያዘ መልስ ለማቅረብ የሚሰጠው የዝግጅት ጊዜ እንደክሱ ክብደትና ውስብስብነት ሚዛናዊ የጊዜ መጠን መሆን ይኖርበታል፡፡ ዛሬ ክሱ ተሰጥቶት ለነገ መልስ መጠበቅ በተዘዋዋሪ የመሰማት መብትን እንደመንፈግ ይቆጠራል፡፡ በመጨረሻም ክሱን የሚሰማው አካል ትክክለኛ ማንነት በማስታወቂያው ላይ መመልከት ይኖርበታል፡፡
የክስ ማስታወቂያ በአካል ስለመስጠት
የጥሪ ማስታወቂያው በይዘቱ በቂ ሊባል የሚችል ቢሆንም ለባለጉዳዩ በአግባቡ እስካልዳረሰው ድረስ የመሰማት መብቱ ተጓድሏል፡፡ ባለጉዳዩ በቅርብ የሚገኝ ከሆነ በተቻለ መጠን መጥሪያው ለራሱ በአካል ሊሰጠው ይገባል፡፡ ከተገቢ ጥረት በኋላ ለማግኘት የማይቻል ከሆነ ማስታወቂያውን ቅርብ በሆነ ቦታ ላይ መለጠፍና ለተወሰነ ጊዜ በተለጠፈበት ቦታ እንዲቆይ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጉዳዩ በሚሰማበት ቀን አለመቅረብ ክርክሩ በሌለበት እንዲቀጥል የሚያደረግ በመሆኑ የመጥሪያ በአግባቡ መድረስ የመስማት መብት አካል ተደርጐ መቆጠር ይኖርበታል፡፡
ክርክርና ማስረጃ የማቅረብ መብት
ክስ የቀረበበት (ባለጉዳይ) ጉዳዩ በተቀጠረበት ቀን በአካል ወይም በወኪሉ ተገኝቶ ክርክሩን የመከታተል፤ መልስ፣ ክርክርና ማስረጃ የማቅረብ ዕድል ሊያገኝ ይገባል፡፡ ይህ መፈጸሙን ማረጋገጥ ክርክሩን የሚሰማው አካል ግዴታ ነው፡፡ መልሱ የሚቀርብበት መንገድ እንደየሁኔታው በቃል ወይም በጽሑፍ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚቀርበው የማስረጃ ዓይነት የቃል (የሰው ምስክር) ወይም የጽሑፍ ማስረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ማስረጃው በ3ኛ ወገን እጅ የሚገኝ ከሆነ ባለጉዳዩ እንዲቀርቡለት በጠየቀ ጊዜ ክርክሩን የሚሰማው አካል እንዲቀርቡ ማድረግ አለበት፡፡
መስቀለኛ ጥያቄ የማቅረብ መብት
ባለጉዳዩ የተቃራኒ ወገን ክስና ማስረጃ በአግባብ ሊደርሰውና ሊመለከተው እንደሚችል ከዚህ በፊት ተገልጿል፡፡ የዚህ ዓላማ በአንድ በኩል ባለጉዳዩ የራሱን መከራከሪያና ማስረጃ በማቅረብ ክሱን በቀጥታ እንዲከላከል ሲሆን በሌላ በኩል የተቆጠረበትን ማስረጃ ማስተባበል እንዲያስችለው ጭምር ነው፡፡
በፍርድ ቤት በሚካሄድ መደበኛ ክርክር መስቀለኛ ጥያቄ የምስክሮችን ተዓማኒነት ለማሳጣትና በአጠቃላይ እውነትን ለማውጣት ውጤታማ መሳሪያ ነው፡፡ ተከሳሹ መስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብ ዕድሉ ተነፍጐት የተሰጠ የምስክርነት ቃል ህጋዊ ብቃቱም አጠያያቂ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን የአስተዳደር ክርክር በዓይነቱና በይዘቱ የፍርድ ቤት ክርክር መልክ ከያዘ ውጤታማ አስተዳደርን ወደ ኋላ መጎተቱ አይቀርም፡፡ ስለሆነም የመስቀለኛ ጥያቄ መቅረት ባለጉዳዩ ውጤታማ መከላከያ እንዳያቀርብ የሚያግደው ካልሆነ በስተቀር ውሳኔ ሰጭው አካል በመብቱ ላይ ገደብ ሊያደርግ ይችላል፡፡b ይሁን እንጂ ምስክርነቱ በቃለ መሀላ ስር የተሰጠ ከሆነ መስቀለኛ ጥያቄ መከልከል አይገባም፡፡ በዚህ ረገድ የ1967ቱ ረቂቅ አዋጅ መስቀለኛ ጥያቄ የማቅርብ መብት ለባለጉዳዩ የሚፈቅድ ግልጽ ድንጋጌ የለውም፡፡ በተቃራኒው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ረቂቅ የአስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ (1993) በአንቀጽ 6 (3)(ሐ) ላይ ይህን መብት በግልፅ አካቷል፡፡
በአስተዳደራዊ ክርክሮች ላይ መስቀለኛ ጥያቄ የማቅረብ መብት ከሞላ ጎደል በሁሉም ህጎችቻን ላይ አልተካተተም፡፡ ልዩ ሁኔታ የሚገኘው በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ 847/2006 ላይ ነው፡፡ በአንቀጽ 39/2/ እንደተመለከተው የዲሲፕሊን ክስ የቀረበበት ሰው የከሳሽን ምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን ክስ በሚሰማበት ወቅት እንዲሁ ግራ ቀኙ መስቀለኛ ጥያቄ ማቅረብ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ በፌደራል መንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን አፈጻጸምና የቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓት ደንብ ቁ. 77/1994 አንቀጽ 17/5/ እንደሰፈረው የከሳሽ ምስክሮችን ተከሳሹ፤ የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮችን የመንግስት መስሪያ ቤቱ ተወካይ፤ የዲሲፕሊን ኮሚቴው የጠራቸውን ተጨማሪ ምስክሮች ደግሞ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች መስቀለኛ ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጠበቃ ተወክሎ የመከራከር መብት
የባለጋራን ክስና ማስረጃ ለማስተባበል የህግ ባለሙያ እገዛ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡ በተለይ ውስብስብ በሆኑ የአስተዳደር ክርክሮች ተካፋይ የሆነ ወገን ካለባለሙያ እገዛ ራሱን በውጤታማ መንገድ ለመከላከል ያለው ዕድል አነስተኛ ነው፡፡ ሆኖም በጠበቃ መወከል መሰረታዊ የመሰማት መብት አካል ተደርጐ አይቆጠርም፡፡ በመብቱ ላይ የሚጣለው ገደብ የራሱ አሳማኝ ምክንያቶች አሉት፡፡
የአስተዳደራዊ ዳኝነት ክርክር ጥብቅ የሆነ የመደበኛ ፍ/ቤቶች ዓይነት የስነ-ስርዓት አካሄድ ሳይከተል በፍጥነት ጉዳዩን ለመቋጨት ያለመ ነው፡፡ የጠበቃ መኖር ክርክሩ የባሰ እንዲወሳሰብና ከተገቢው ጊዜ በላይ እንዲንዛዛ በማድረግ የክርክሩን ኢ-መደበኛ ባህርይ ያጠፋዋል፡፡ በአጠቃላይ አነጋገር በጠበቃ ውክልና ከሚታገዝ ይልቅ ባለጉዳዩ ራሱ የሚከራከርበት አስተዳደራዊ ክርክር በአጭር ጊዜ እልባት ያገኛል፡፡ ያም ሆኖ ግን ክርክር የሚካሄድበት ጉዳይ በባሉጉዳዩ መብትና ጥቅም ላይ ሊኖረው ከሚችለው አሉታዊ ውጤት አንጻር ማለትም የክርክሩን ክብደትና ውስብስነት መሰረት አድርጐ እንደየሁኔታው በጠበቃ የመወከል ጥያቄን ማስተናገድ ያስፈልጋል፡፡
ምክንያታዊ ውሳኔ
ዜጐች በሰውነታቸውና በንብረታቸው ላይ እርምጃ ሲወሰድ ከመንግስት ምክንያት ይሻሉ፡፡ አንዳችም ምክንያት የሌለው ውሳኔ የአስተዳደር በደል መገለጫ ነው፡፡ ኢ-ፍትሐዊነት በሁለት መልኩ ይገለጻል፤ የመጀመሪያው ምክንያት ሳይጠቀስ በደፈናው ውሳኔ ሲሰጥ፣ ሁለተኛው ደግሞ ውሳኔው በራሱ ፍርደገምድል፣ ሚዛናዊነት የጐደለውና በአሳማኝ ምክንያት ያልተደገፈ ሲሆን፡፡
ለውሳኔ ምክንያት መስጠት በአስተዳደር ህግ ውስጥ ጉልህ ስፍራ እያያዘና እያደገ የመጣ መሰረተ ሀሳብ ነው፡፡ ያም ሆኖ ከአሜሪካው የአስተዳደር ስነስርዓት በስተቀር በእንግሊዝ ሆነ በህንድ ምክንያት እንዲሰጥ የሚያስገድድ በሁሉም የአስተዳደር አካላት ተፈጻሚ የሆነ ጠቅላላ ደንብ የለም፡፡ ሆኖም አልፎ አልፎ ማቋቋሚያው አዋጅ ለአስተዳደራዊ ውሳኔ ምክንያት እንዲሰጥ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣል፡፡
አስተዳደራዊ ውሳኔ ሊኖረው የሚገባውን ይዘትና ቅርጽ በተመለከተ በ1967 ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 13 እንዲሁም በፌደራሉ ረቂቅ አዋጅ (1993 ዓ.ም.) አንቀጽ 32 ላይ ቅድመ ሁኔታዎቹ ተዘርዝረዋል፡፡ በዚሁ መሰረት አስተዳደራዊ ውሳኔ በጽሑፍ መሰጠት ያለበት ሲሆን ውሳኔውም የክርክሩን ፍሬ ነገር፣ የማስረጃዎች ፍሬ ጉዳይና ምንጭ፣ የነገሩን ጭብጥ አወሳሰን እንዲሁም በውሳኔው መሰረት ተመስርቶ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ የሚያመለክት መሆን ይኖርበታል፡፡ ምንም እንኳን በረቂቆቹ ላይ ‘ምክንያት’ የሚለው ቃል በግልጽ ባይጠቀስም የውሳኔ ምክንያትን የሚያያቋቁሙ ሁኔታዎች የተካተቱ እንደመሆኑ ምክንያት መስጠት እንደአስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጧል ማለት እንችላለን፡፡
በአንዳንድ አዋጆች ላይ ውሳኔን በምክንያት ማስደገፍ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ለአብነት የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁ. 980/2008 አንቀጽ 6/2/ የንግድ ምዝገባ ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ መዝጋቢው አካል ምክንያቱን ገልጾ ለአመልካቹ ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት፡፡
ከቀረጥ ዋጋ አወሳሰን ጋር በተያያዘ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ተጨማሪ መግለጫ ወይም ሰነድ ከዲክላራሲዮን አቅራቢው ከተቀበለ በኋላ ስለግብይት ዋጋው ትክክለኛነት ያለውን ጥርጣሬ ማስወገድ ካልቻለ ወይም ዲክላራሲዮን አቅራቢው ምላሽ ካልሰጠ በጉምሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀጽ 90 መሰረት ዋጋውን መወሰን እንዳልተቻለ ይቆጠራል፡፡ በዚሁ መሰረት የቀረበው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ተቀባይነት ያላገኘበት ምክንያት በጽሑፍ ለአስመጭው ወይም ለወኪሉ ይገለጽለታል፡፡c
በነዳጅ አቅርቦት ስራ ለመሰማራት የተጠየቀ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ተቀባይነት ካላገኘ ምክንያቱ ለአመልካቹ ይገለጽለታል፡፡d
የስደተኝነት ዕውቅና እንዲሰጥ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት ቢያገኝም ባያገኝም ውሳኔው ለአቅራቢው በጽሑፍ መገለጽ አለበት፡፡e


MUHAJER SEMAN የፍርድ ቤቶች የአጣሪ ዳኝነት።

የፍርድ ቤቶች የአጣሪ ዳኝነት

የፍርድ ቤቶች የአጣሪ ዳኝነት ስልጣንየዳኝነት ስልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ እንደሆነ የሚደነግገው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 79/1/ አጣሪ ዳኝነትን እንደሚጨምር አይጠቁምም፡፡ በህገ መንግስቱ ላይ የፌደራል የመጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ከክልሎች ውክልና ጋር በተያያዘ በስም ቢጠቀሱም የስልጣናቸው ምንጭ ህገ መንግስቱ ሳይሆን የተወካዮች ም/ቤት የሚያወጣው ህግ እንደሆነ በአንቀጽ 78/2/ ተመልክቷል፡፡ በአንጻሩ ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ የሚመነጨው የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የሰበር ስልጣን ከፊል ዳኝነታዊ ስልጣን ያላቸው አካላት የሚያስተላልፉትን ውሳኔ ህጋዊነት ለማጣራት ያስችለዋል፡፡ ይህ ስልጣን ከሁሉም የፌደራልና የክልል ፌደራል ፍርድ ቤቶች (የክልል የሰበር ችሎቶችን ሳይጨምር)በዓይነቱ የተለየና ብቸኛ ነው፡፡የፌደራል ፍ/ቤቶችመደበኛ ፍርድ ቤቶች የስልጣንን ህጋዊነት በሁለት ዓይነት መንገድ ይቆጣጠራሉ፤ በመደበኛ የፍትሐብሔር ክስ እና በአስተዳደራዊ ይግባኝ፡፡ መንግስት ተከራካሪ በሚሆንባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮች በርካታ የአስተዳደር ህግ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ በተለይም ከውል ውጪ ኃላፊነት፣ ከንብረት ህግ እና በከፊል ከውል ህግ የሚመዘዙ በርካታ የህጋዊነት ጥያቄዎች በተዘዋዋሪም ቢሆን አስተዳደሩ ለህግ እንዲገዛ ያስገዱዱታል፡፡ ፍ/ቤቶች ጠቅላላ ከሆነው መደበኛ ስልጣናቸው በተጨማሪ የአስተዳደሩን ተግባራት ህጋዊነት በይግባኝ እንዲያጣሩ በተለያዩ ዝርዝር ህጎች ላይ ተጨማሪ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ በፍሬ ነገርና በህግ ጉዳይ ላይ የሚፈቀድ ይግባኝ ከዜጋው መብት አንጻር ከአጣሪ ዳኝነት የበለጠ ጠቀሜታ አለው፡፡ ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ ነገሩን እንደ አዲስ የማየትና ክርክሩ ከተቋጨ በኋላ በራሱ ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተለጠጠ ስልጣን ያጎናጽፈዋል፡፡ አጣሪ ዳኝነት ግን ህጋዊነትን ከማጣራት አይዘልም፡፡ የአስተዳደራዊ ውሳኔን በመቃወም ለፌደራል ፍ/ቤቶች ይግባኝ የማቅረብ መብት ከሚፈቅዱ ድንጋጌዎች መካከል የሚከተሉት በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትመረጃ ከማግኘት መብት ጋር በተያያዘ መረጃ ተጠይቆ መረጃውን የያዘው አካል በመከልከሉ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ይግባኝ ከቀረበ በኋላ እንባ ጠባቂው በሚሰጠው ውሳኔ ላይaየአካባቢ ተቆጣጣሪዎች በሚሰጡት ውሳኔ እንዲሁም እንዲሁም በአካባቢ ላይ የደረሰ ጉዳትን አስመልክቶ ለአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር አቤቱታ ቀርቦ ሚኒስቴሩ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ bየፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትከጥራት ጋር በተያያዘ ቡና የተያዘበት ወይም መጋዘኑ የታሸገበት ሰው ለእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ወይ አግባብ ላለው የክልል መንግስት አካል ቅሬታ አቅርቦ ተቀባይነት ካጣcየጀነቲክ ቁስ ማስተላለፊያ መደበኛ ውል አፈጻጸምን አስመልክቶ የሚነሳ ክርክርdለሰሊጥ ወይም ነጭ ቦሎቄ አቅራቢነት፣ ላኪነት ወይም አገልግሎት ሰጪነት የብቃት ማረጋገጫ ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ የህግ አተረጓጎምን በተመለከተ ወይም ተፈቅዶለት በዚህ ንግድ የተሰማራ ሰው ከጥራት ጋር በተያያዘ ሰሊጥ ወይም ነጭ ቦሎቄ ተይዞበት ለሚኒስትሩ ወይም አግባብ ላለው የክልል መንግስት አቤቱታ አቅርቦ ተቀባይነት ካጣeየጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት የቀረበ ማመልከቻ ተቀባይነት እንዲያጣ ወይም ፈቃድ የተሰጠው ጠበቃ በዲሲፕሊን ጥፋት ምክንያት ቅጣት በመጣል በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የተወሰደ እርምጃ (በህግ ጉዳይ ላይ ብቻ)fየሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበር ምዝገባ ባለመፍቀድ እንዲሁም ለስራ ውል መታገድ በቂ ምክንያት አለመኖሩን በመግለጽ በሚሰጠው ውሳኔ እና የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪ የሚሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወምgየዕፅዋት አዳቃዮች መብት መስጠትን፣ መከልከልን፣ መሰረዝን ወይም መገደብን በተመለከተ በሚሰጥ ውሳኔ ላይhየምርት ገበያ ባለስልጣን በሚሰጣቸው በአዋጁ በተመለከቱ ውሳኔዎችiየፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ ውድቅ በማድረግ ወይም በመሰረዝ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚሰጥ ውሳኔjየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ፈቃድ በመሰረዝ በሚሰጠው ውሳኔ እንዲሁም ባንኩ የሾመው ሞግዚት በሚያስተላልፈው ውሳኔkየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ፈቃድ በመሰረዝ በሚሰጠው ውሳኔlየፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ስልጣን በቀጥታ ከህገ መንግስቱ ይመነጫል፡፡ ሆኖም የስልጣኑን ወሰን የሚያሰምረው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ ሀ የአማርኛውና እንግሊዝኛው ቅጂ ግልጽ መፋለስ ይታይበታል፡፡ በአማርኛው ንባብ የሰበር ችሎት መሰረታዊ ‘የህግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ’ የማረም ስልጣን ይኖረዋል፡፡ (ሰረዝ የተጨመረ) የእንግሊዝኛው ቅጂ ደግሞ Over any final court decision የሚል አገላላጽ በመጠቀም ስልጣኑን ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ በሰጠባቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ ይገድበዋል፡፡የድንጋጌውን ይዘት ዝርዝር የሚወስነው ህግ ከእንግሊዝኛው ቅጂ ጋር ይስማማል፡፡ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁ. 25/1988 አንቀጽ 10 የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የሰበር ስልጣን የሚያገኝባቸው ሶስት ጉዳዮች ተዘርዝረዋል፡፡ እነዚህም፤የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳዮችየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳዮችየክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት መደበኛ ችሎት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳዮችበሶስቱም ጉዳዮች በውሳኔ ሰጭነት የተጠቀሱት ተቋማት መደበኛ ፍርድ ቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ረ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ ሀ የእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ court የሚለው ቃል እንዲሁ ይህንኑ ሀሳብ ያንጸባርቃል፡፡ ሆኖም የአማርኛው ንባብ ውሳኔ ሰጭውን በዝምታ አልፎታል፡፡ ላይ ላዩን ሲታይ ዝምታው ለህገ መንግስታዊ ትርጉም በር የከፈተ አይመስልም፡፡ ‘የመጨረሻ ውሳኔ’ የሚለው አገላለጽ ፍርድ ቤትን ታሳቢ አድርጓል ቢባል ብዙዎችን ያስማማል፡፡ሆኖም ችግሩ ከቋንቋ አጠቃቀም ያልዘለለ የሚመስለው የአንቀጽ 80/3/ ሀ ድንጋጌ በተግባር ህገ መንግስታዊ ጥያቄ አስነስቶ የሰበር ችሎትን የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን አስፍቶታል፡፡ በሰ/መ/ቁ. 43511m ከአዋጅ ውጪ የተወረሱ ንብረቶችን በተመለከተ ከፊል ዳኝነታዊ ስልጣን የተሰጠው የፕራይቬይታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ በቀጥታ በሰበር እንዲታይ አቤቱታ ቢቀርብም አጣሪ ችሎቱ ጉዳዩ አስተዳደራዊ መሆኑን በመጠቆም ውድቅ አድርጎታል፡፡ ሆኖም በመዝገቡ ላይ አመልካች ሆነው የቀረቡት አቤቱታ አቅራቢዎች የውሳኔውን ህገ መንግስታዊነት በመሞገት ለህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ አቤቱታ አስገቡ፡፡ አጣሪውም ለጥያቄያቸው አዎንታዊ ምላሽ ባለመስጠቱ የመጨረሻ አማራጫቸውን በመጠቀም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አመለከቱ፡፡ ም/ቤቱ የችሎቱን ስልጣን በማረጋገጥ መዝገቡን ወደ ሰበር ችሎት መለሰው፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የቦርዱን ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን እንዳለው በማረጋገጥ የተሰጠው ይህ የም/ቤቱ ውሳኔ ‘የመጨረሻ ውሳኔ’ በሚል በህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ ሀ ላይ የተቀመጠውን አገላለጽ ከእንግሊዝኛ ቅጂ ፍጹም የተለየ ይዘትና መልዕክት ሰጥቶታል፡፡ በውጤቱም ከፍርድ ቤት ውጭ ያሉ ከፊል የዳኝነት አካላት ላይ የሰበር ችሎት የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን እንዳለው አረጋግጧል፡፡የም/ቤቱ ውሳኔ ህገ መንግስታዊ ፋይዳው ስር ነቀልና መሰረታዊ ነው፡፡ የስር ፍ/ቤቶችን የህግ ስህተት በማረም ብቻ ተወስኖ የነበረው የሰበር ችሎት በም/ቤቱ ‘በተጨመረለት’ ስልጣን ከፊል ዳኝነታዊ ስልጣን የተሰጣቸው የአስተዳደር አካላት የሚያስተላልፉትን ውሳኔ ጭምር የማረም የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ችሎቱም ዳኝነታዊ የአስተዳደር ውሳኔዎችን ማረም ህገ መንግስታዊ ሚናው እንደሆነ በሌሎች ሁለት መዝገቦች በሰጣቸው ውሳኔዎች በተግባር አረጋግጧል፡፡በሰ/መ/ቁ. 92546n የድሮው ፍትሕ ሚኒስቴር የአሁኑ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የዲሲፕሊን ውሳኔ በቀጥታ ለሰበር ችሎት ቀርቦ ተሸሯል፡፡ አቤቱታ አቅራቢው በሚኒስትሩ የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደው በዓቃቤ ህግ ላይ ሲሆን ጉዳዩ በሰበር ችሎት ከመስተናገዱ በፊት በሌላ ፍርድ ቤት አልታየም፡፡ በመዝገቡ ላይ የችሎቱ የዳኝነት ስልጣን አከራካሪ ጭብጥ ሆኖ ባይወጣም የህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ ሀ እና አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 10 ተጠቅሶ የቀረበውን አቤቱታ ችሎቱ መቀበሉ ሲታይ የአጣሪ ዳኝነት ስልጣኑ ጠንካራ መሰረት እየያዘ እንደመጣ አስረጂ ነው፡፡ በሰ/መ/ቁ. 61221 ቅጽ 14o የተያዘው አቋም ይህንን ሀሳብ ያጠናክራል፡፡ በዚህ መዝገብ በሰፈረው የህግ ትርጉም በፍርድ ቤት እንዳይታዩ በመጨረሻ ማሰሪያ ድንጋጌ (finality clause) ገደብ የተደረገባቸው ውሳኔዎች ሳይቀር በችሎቱ የአጣሪ ዳኝነት ስር እንዲወድቁ ተደርገዋል፡፡ ጉዳዩ የታየው አዋጅ ቁ. 714/2003 እና 715/2003 ከመውጣታቸው በፊት ሲሆን ቀድሞ በነበሩት የጡረታ ህጎች የማህበራዊ ዋስትና ጉባኤ ውሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ በይግባኝ ሆነ በቀጥታ ክስ በመደበኛ ፍ/ቤቶች ሊታይ አይችልም፡፡በሰ/መ/ቁ. 61221 የሰበር አቤቱታ የቀረበው የጉባዔውን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ ሆኖም በችሎቱ የዳኝነት ስልጣን ላይ በተጠሪ በኩል ተቃውሞ በመቅረቡ የስልጣን ምንጭ አከራካሪ ጭብጥ ሆኖ ወጥቷል፡፡ ይህንን በማስመልከት ህገ መንግስቱን እና አዋጅ ቁ. 25/88 በማጣቀስ የሚከተለው የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡ጉዳዩ በተነሳበት ጊዜ ስራ ላይ በነበረው ሕግ አግባብ ማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ነው ከተባለ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 በተመለከተው አግባብ ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ ከማቅረብ የሚከለክል ሕጋዊ አግባብ የለም፡፡የከተማ ፍ/ቤቶችበአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ የተቋቋሙት የከተማ ፍርድ ቤቶች በውስን ጉዳዮች ላይ ቢሆንም የማይናቅ የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን አላቸው፡፡ ስልጣናቸውን በሚወስኑት ህጎች ላይ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች መካከል የሚከተሉትp በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአጣሪ ዳኝነት የሚታዩ ናቸው፡፡የከተማውን መሪ ፕላን አፈጻጸም የሚመለከት የይዞታ ባለመብትነት፣ የፈቃድ አሰጣጥ ወይም የቦታ አጠቃቀምን በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮችከከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የመቆጣጠር ስልጣንና ተግባር ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችበየከተሞቹ ቻርተር ላይ በተመለከቱት የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ክሶችየከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ወይም በከተማው አስተዳደር ባለቤትነት ስር ያሉ ተቋማት የሚገቧቸውን አስተዳደራዊ ውሎች በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮችበከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ወይም በስሩ ባሉ ተቋማት መካከል የሚነሱ ክርክሮችየከተማው አስተዳደር ከሚያስተዳድራቸው የመንግስት ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችበህግ ከተሰጣቸው የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን በተጨማሪ በከፊል ጉዳዮች አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን በይግባኝ ያያሉ፡፡ ለምሳሌ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ቅሬታ ሰሚ ጉባዔ በሚሰጠው ውሳኔq የመጀመሪያና የይግባኝ ስልጣን አላቸው፡፡የከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ክልል በህጉ ላይ በወጉ አልተሰመረም፡፡ ህግ አውጭው ‘በተመለከተ…በተያያዘ…’ በሚል የተጠቀመው አገላለጽ መብት ጠያቂውን ሆነ ፍርድ ቤቶችን ያደናግራል፡፡ የዳኝነት ስልጣን ሊወሰን የሚገባው በክስ ምክንያት፣ ፍርድ ቤቱ በሚሰጠው መፍትሄ ወይም በተከራካሪዎች ማንነት ነው፡፡ ለምሳሌ የይዞታ ባለመብትነትን በተመለከተ እንዲሁም ከአስፈፃሚ አካላት የመቆጣጠር ስልጣንና ተግባር ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮች እንደ ሁኔታው በፌደራል ወይም በከተማ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር ይወድቃሉ፡፡ ይዞታን የሚመለከት ክስ በሁከት ይወገድልኝ ወይም በመፋለም ክስ አሊያም ደግሞ በይዞታ ላይ ለደረሰ ጉዳት ካሳ በመጠየቅ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ከግንባታ ፈቃድ ወይም ስም ከማዛወር አስተዳደራዊ ግዴታ ጋር በተያያዘም ይዞታን የሚመለከት ጥያቄ ይነሳል፡፡ ከዚህ አንጻር በደፈናው ‘በተመለከተ…’ በሚል የተደለደለው የዳኝነት ስልጣን የመደበኛ እና የከተማ ፍ/ቤቶችን ድርሻ በአግባቡ አይለይም፡፡ህጉ ግልጽነት ቢጎድለውም ከሰበር ችሎት አካሄድ እና የህግ አውጭው ሀሳብ በመነሳት የከተማ ፍ/ቤቶች መደበኛ የፍትሐብሔር የዳኝነት ስልጣን እንዳልተሰጣቸው ድምዳሜ ላይ መድረስ እንችላለን፡፡ ህግ አውጭው እነዚህን ፍ/ቤቶች ሲያቋቁም ከተወሰኑት በግልፅ ከተነገሩት በስተቀር መደበኛውን የፍትሐብሔር ዳኝነት አላስተላለፈላቸውም፡፡ የሰበር ችሎት በበርካታ መዝገቦች ያንጸባረቀው አቋም ከዚህ ሀሳብ ጋር ይስማማል፡፡ ይህ ከተባለ በኋላ ግን ከላይ በቀረበው ዝርዝር ውስጥ ህግ አውጭው የወሰነው የዳኝነት ስልጣን ምን መልክ እንዳለው መለየት ያስፈልጋል፡፡ራሱን የቻለ የአስተዳደር ህግ ስርዓት ባላቸው አገራት በፍርድ ቤት የሚታዩ ጉዳዮች ሶስት ዓይነት ናቸው፤ የፍትሐብሔር፣ የወንጀል እና የአስተዳደር፡፡ በፈረንሳይ የአስተዳደር ክርክሮች ከመደበኛ ፍ/ቤቶች ተለይተው በተቋቋሙ የአስተዳደር ፍ/ቤቶች አማካይነት ይዳኛሉ፡፡ በጀርመን ራሱን ችሎ በተለይ በተቋቋመ የአስተዳደር ፍ/ቤት ይታያሉ፡፡ ከስልጣን ክፍፍል አንጻር መደባቸው ሲታይ የአስተዳደር ፍ/ቤቶች በፈረንሳይ በስራ አስፈፃሚው ስር የሚገኙ ሲሆን በጀርመን ግን በዳኝነት አካሉ የታቀፉ ናቸው፡፡ በእንግሊዝ የፍትሐብሔር ክርክሮችን የሚያስተናግዱት መደበኛ ፍ/ቤቶች የአስተዳደር ክርክሮችንም ደርበው ይዳኛሉ፡፡ በእርግጥ አስተዳደር ነክ ጥያቄዎች የሚቀርቡት ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢሆንም ፍ/ቤቱ ራሱን የቻለ የተለየ መዋቅር የለውም፡፡ በሶስቱም አገራት በመንግስትና በግለሰብ መካከል የሚካሄዱ ክርክሮች የሚዳኙበት መንገድ ቢለያያም አንድ ነገር ያመሳስላቸዋል፡፡ ይኸውም የዳኝነት ስልጣናቸው ዓይነት አጣሪነት (supervisory) ነው፡፡ የዚህ ስልጣን ወሰን የአስተዳደሩን ተግባራት ህጋዊነት ማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ያለፉ የፍትሐብሔር ክርክሮችን መደበኛ ፍ/ቤቶች ይረከባሉ፡፡ ለምሳሌ አንድ የአስተዳደር ተቋም ከህግ የመነጨ ስልጣኑን በመጠቀም እርምጃ ሲወስድ ክርክሩ በአጣሪነት ዳኝነት ስር ይወድቃል፡፡ እንደማንኛውም ግለሰብ በሚፈጽማቸው የግል ተግባራት ሲከሰስ (ለምሳሌ የተቋሙ መኪና በአካል ወይም ንብረት ላይ ጉዳት በማድረሱ ከውል ውጭ በሚደርስ ኃላፊነት ካሳ ሲጠየቅ) ደግሞ መደበኛ ፍ/ቤቶች በፍትሐብሔር የዳኝነት ስልጣናቸው ያዩታል፡፡በከተማ ፍ/ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ስር ከተዘረዘሩት መካከል የይዞታ ባለመብትነትን በምሳሌነት ብንወስድ ከላይ ለመጠቆም እንደተሞከረው ጉዳዩ የሚታይበት ፍ/ቤት የሚለየው በክሱ ይዘት ነው፡፡ ከፍትሐብሔር ውጭ በአስተዳደሩ ላይ ሊቀርብ የሚችለው ክስ ህጋዊነት የሚጣራበት ክስ ነው፡፡ ይህም የሚያደርሰን መደምደሚያ የከተማ ፍርድ ቤቶች በህግ የተወሰነላቸው የዳኝነት ስልጣን ዓይነት የአጣሪ ዳኝነት (judicial review) ስልጣን እንደሆነ ነው፡፡

MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE

የአስተዳደርህገ መንግስታዊ የመሰማት መብት?

ህገ መንግስታዊ የመሰማት መብት?

ገ መንግስታዊ የመሰማት መብት?

የተፈጥሮ ፍትሕ በእንግሊዝና ሌሎች ኮመን ሎው አገራት በዳኞች የዳበረ የፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርህ ነው፡፡ ይህ መርህ በህግ በግልጽ እንደ ቅድመ ሁኔታ ባይቀመጥም ዳኞች ተፈጻሚ እንዳያደርጉት አያግዳቸውም፡፡ በአሜሪካ እንዲሁ ህገ መንግስታዊ ዕውቅና ያገኘው ዱ ፕሮሰስ ኦፍ ሎው (Due Process of Law) በመባል የሚታወቀው ህገ መንግስታዊ መርህ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን የሚገዛ ልዩ ህግ ባይኖርም እንኳን ፍርድ ቤቶች እንደ አግባብነቱ ተፈጻሚ ያደርጉታል፡፡ ሆኖም በእነዚህ ሁለት አገራት ሆነ በሌሎችም ዘንድ አስተዳደር የሚመራበት ስነ ስርዓት ምንጩ በህግ አውጪው የሚወጣ ህግ ነው፡፡

ግልጽ የህግ ድንጋጌ ካለ የስነ-ስርዓት ጉድለት ያለበት ውሳኔ በፍርድ ቤት ሊሻር ወይም ሊሰረዝ እንደሚገባው አያጠራጥርም፡፡ አስገዳጅ የህግ ድንጋጌ ከሌለስ? ፍርድ ቤቶቻችን እንደ እንግሊዝና አሜሪካ ፍርድ ቤቶች ፍትሐዊ የውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎችን ማዳበርና ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው? ካለባቸውስ አቋማቸው ህገ መንግስታዊ መሰረት አለው? በአስተዳደራዊ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት የመሰማት መብት እንዲሁም ኢ-አድሎአላዊነት መርህ በህግ በግልጽ ባልተደነገገበት ሁኔታ የስነ-ስርዓት ጉድለት ያለበት አስተዳደራዊ ውሳኔ ዕጣ ፋንታ መወሰን በብዙ መልኩ ከባድ ነው፡፡

በአንድ በኩል ፍርድ ቤቶች የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት መብት የማረጋገጥ ህገ መንግስታዊ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ህጉን ከማንበብና ከመተርጎም ባለፈ ህግ መጻፍ ህገ መንግስታዊ ሚናቸው አይፈቅድላቸውም፡፡ በዚህ መልኩ የሚፈጠረው ‘ህገ መንግስታዊ አጣብቂኝ’ ብርታትና ጥንቃቄ ካልታከለበት በቀላሉ አይፈታም፡፡ በተጨማሪም ‘መርህ’ በተጨባጭ ‘መሬት ሲወርድ’ ከልዩ ሁኔዎች ጋር ሊጣጣምና የተፈጻሚነት ወሰኑ በአግባቡ ሊሰመር ይገባል፡፡ የመሰማት መብት የግድ የሚልበት ሁኔታ ቢኖርም ከተግባራዊ ፋይዳውና ውጤታማ አስተዳደር አንጻር የሚገደብባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ በተጨማሪም የተፈፃሚነቱ ወሰን የግለሰብ መብት ወይም ጥቅም በሚነካ የዳኝነታዊ ባህርይ ባለው አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ ብቻ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየን አስቸጋሪው ስራ የፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎችን በጠቅላላው መቀበሉ ሳይሆን እንደ ጉዳዩ አይነት ልዩ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የተፈጻሚነቱን አድማስ መለየቱ ላይ ነው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 43511a በ2005 ዓ.ም. በሰጠው ፈር ቀዳጅ የህግ ትርጉም መሰረት አስገዳጅ የህግ ድንጋጌ ባይኖርም ከፊል የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል የመሰማት መብትን የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ የችሎቱን አቋም በጥልቀት ለመረዳት በሐተታው ክፍል የሰፈረውን የሚከተለውን አስተያየት ማየቱ ተገቢ ነው፡፡…የመሰማት መብት በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ሊከበር የሚገባው መብት ነው፡፡ የመሰማት መብት ከመጀመሪያው ክርክር ጀምሮ እስከመጨረሻው የዳኝነት ሰጪ አካል መከበር ያለበት ስለመሆኑ በሕገ መንግስቱና ስለ ክርክር አመራር በተደነገጉት እንደፍትሐብሔር ስነ ስርአት አይነት ሕጎች ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡

የችሎቱ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ዜጎች ሀሳባቸው ሳይደመጥ መብትና ጥቅማቸውን የሚጎዳ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዳይሰጥባቸው ከለላ በማጎናጸፍ ረገድ ህገ መንግስታዊ ፋይዳው ‘ታሪካዊ’ ሊሰኝ የሚችል ነው፡፡ ከዚያም አልፎ ለአገራችን የአስተዳደር ህግ ዕድገት ችሎቱ ካደረጋቸው አስተዋጽኦዎች መካከል ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል፡፡ በእርግጥ የውሳኔው ፋይዳ ብቻውን በቁሙ መለካት በተግባር ያስከተላቸውን ለውጦች በማጋነን ያስተቻል፡፡ የሰ/መ/ቁ. 43511 አስተዳደሩ አካሄዱን ከችሎቱ አቋም ጋር እንዲያስተካክል በዚህም የመሰማት መብትን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ አካል አድርጎ እንዲያቅፍ የፈጠረው ጫና ሆነ በተግባር ያስከተለው ተጨባጭ ለውጥ የለም፡፡ አስገዳጁን የህግ ትርጉም መቀበልና መተግበር ያለባቸው የስር ፍርድ ቤቶችም ቢሆኑ በአስተዳደራዊ ክርክሮች የመሰማት መብትን በትጋት እንዲያስከብሩ የለውጥ ምንጭ አልሆነላቸውም፡፡ ምናልባትም ውሳኔው ስለመኖሩ ራሱ ገና አልሰሙ ይሆናል፡፡ የሰበር ውሳኔዎች የተደራሽነት ችግር እንዲሁም በውሳኔዎቹ ላይ ጠንካራ ምሁራዊ የሀሳብ ልውውጥ ባህል አለመዳበር በርካታ አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች በቅጾች መጽሐፍ ውስጥ ተቀብረው እንዲረሱ ያደርጋቸዋል፡፡

የሰ/መ/ቁ. 43511 ከህገ መንግስታዊ ፋይዳው ባሻገር ክርክሩ የተጓዘበት መስመር ትኩረት ይስባል፡፡ የክርክሩ መነሻ አመልካቾች ከአዋጅ ውጪ የተወረሰ ቤት እንዲመለስላቸው ለኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ያቀረቡት አቤቱታ ሲሆን ኤጀንሲውም ተጠሪ ምላሽ እንዲሰጡበት ካደረገ በኋላ ማስረጃና ክርክሩን ሰምቶ ቤቱ እንዲመለስላቸው ወስኗል፡፡ በውሳኔው ባለመስማማት ተጠሪ ለኤጀንሲው ቦርድ ይግባኝ በማቅረባቸው ቦርዱ የኤጀንሲውን ውሳኔ ሽሮታል፡፡ ከመሻሩ በፊት ግን አመልካቾችን ጠርቶ ክርክራቸውን አልሰማም፡፡

በመቀጠል አመልካቾች የመሰማት መብታቸው አለመጠበቁን በመግለጽ በቀጥታ የሰበር አቤቱታ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰ/ችሎት ያቀረቡ ቢሆንም አጣሪ ችሎቱ የቦርዱን ውሳኔ የማረም ስልጣን እንዳልተሰጠው በመግለጽ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ አመልካቾች ተስፋ ባለመቁረጥ ጉዳዩ ህገ መንግስታዊ ትርጉም እንደሚያስነሳ በመጠቆም ለህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ አመለከቱ፡፡ እዛም ተቀባይነት አጡ፡፡ አሁንም ሰሚ ፍለጋ ‘አቤት!’ ማለታቸውን ባለማቆም ጉዳያቸውን እንዲያይላቸው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ አቀረቡ፡፡ በመጨረሻ ጥያቄያቸው ፍሬ አግኝቶ የአጣሪ ችሎቱ ውሳኔ ተሻረ፡፡

አመልካቾች ተስፋ ባለመቁረጥ እስከ ፌዴሬሽን ም/ቤት ድረስ ዘልቀው ድል መጎናጸፋቸው በራሱ የተለየ ስሜት ቢያጭርም በተለየ መልኩ ትኩረት የሚስበው ግን የክርክሩ ሂደት ሳይሆን የም/ቤቱ ውሳኔ ይዘት ነው፡፡ የሰበር ችሎት የዳኝነት ስልጣንን በማስፋት አዲስ ህገ መንግስታዊ መልክ ያላበሰው ይኸው ውሳኔ የሰበር ችሎት የቦርዱን መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን እንዳለው አረጋግጧል፡፡ የም/ቤቱ ህገ መንግስታዊ ትርጓሜ መነሻ ያደረገው የኤጀንሲው ቦርድ ዳኝነታዊ ስልጣን ነው፡፡ ስለሆነም ቦርዱ የዳኝነት መሰል አካል (quasi judicial body) በመሆኑና ይህ አካል የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር ስልጣኑ ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለው፡፡

የስልጣን ጥያቄው እልባት ካገኘ በኋላ መዝገቡ ከፌዴሬሽን ም/ቤት ወደ ሰበር ችሎት ሲመለስ የቦርዱ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት መሰረታዊ ጭብጥ ሆኖ ተነስቷል፡፡ ጭብጡን ለመፍታት ችሎቱ የቦርዱን የማቋቋያ አዋጅb የተመለከተ ቢሆንም በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ቦርዱ የተከራካሪዎችን የመሰማት መብት እንዲጠብቅ የሚያስገድድ ድንጋጌ አላገኘም፡፡

በአስተዳደራዊ ክርክሮች ላይ የመሰማት መብት የሚጠብቅ ህግ በሌለበት ሁኔታ ውሳኔው ሰጭው አካል በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት መብቱን እንዲያከብር ግዴታ መጫን ለችሎቱ ፈታኝ ስራ እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ ምክንያቱም ከህግ የመነጨ ግዴታ በሌለበት ቦርዱ የመሰማት መብት መርሆዎችን እንዲከተል ማስገደድ በውጤቱ የችሎቱን ተግባር ከህግ መተርጎም ወደ ‘ህግ መጻፍ’ ያሸጋግረዋል፡፡ ስለሆነም ችሎቱ በስልጣን ክፍፍል መርህ የተሰመረውን ድንበር ሳይሻገር በራሱ የዳኝነት ስልጣን ዛቢያ ውስጥ ሆኖ ውሳኔውን በአሳማኝ ምክንያት ማስደገፍ አለበት

WELCOME TO MUHAJER SEMAN SURAFEL WEBSITE HOME

Definitions of the Constitution

CRIMINAL PROCEDURE RULES AND DISCIPLINE PROCEDURES CRIMINAL PROCEDURE CODES

የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ

የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ theory demands that all public servants, elected or nonelected, be accountable to the people. Obviously, this requires the creation of certain oversight mechanisms so that administrative behavior can be watched and controlled.aከሁሉም ስልጣንን የመቆጣጠር ኃላፊነትና ግዴታ ከተጣለባቸው ተቋማት መካከል የህዝብ ተወካዮች ስራ አስፈፃሚውንና በስሩ ያሉትን አስፈፃሚ አካላት በቅርበት የመከታተልና የመቆጣጠር አይነተኛ አደራና ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ድምዳሜው ከውክልና ዲሞክራሲ (representative democracy) መርህ ይመነጫል፡፡ ይህ መርህ ከተጠያቂነት ጋር ያለውን ትስስር አሜሪካዊው የፖለቲካ ሳይንስ እና የአስተዳደር ህግ […]

የስልጣን ቁጥጥር: ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ